1
የዮሐንስ ወንጌል 11:25-26
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ኢየሱስም “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ ሕያው የሆነና በእኔ የሚያምን ሁሉ ለዘለዓለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽኝ?” አላት።
Compară
Explorează የዮሐንስ ወንጌል 11:25-26
2
የዮሐንስ ወንጌል 11:40
ኢየሱስ “ካመንሽ የእግዚአብሔርን ክብር እንደምታዪ አልነገርሁሽምን?” አላት።
Explorează የዮሐንስ ወንጌል 11:40
3
የዮሐንስ ወንጌል 11:35
ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።
Explorează የዮሐንስ ወንጌል 11:35
4
የዮሐንስ ወንጌል 11:4
ኢየሱስም ሰምቶ “ይህ ሕመም ለሞት አይሰጥም፤ ይልቁንም ለእግዚአብሔር ክብር መገለጫ ነው፤ የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ነው” አለ።
Explorează የዮሐንስ ወንጌል 11:4
5
የዮሐንስ ወንጌል 11:43-44
ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ “አልዓዛር ሆይ! ና፥ ወደ ውጭ ውጣ፤” ብሎ ጮኸ። ሞቶ የነበረውም ሰው እጆቹና እግሮቹ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፈቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ። ኢየሱስም “ፍቱትና ይሂድ፤ ተዉት፤” አላቸው።
Explorează የዮሐንስ ወንጌል 11:43-44
6
የዮሐንስ ወንጌል 11:38
ኢየሱስም በድጋሚ በጥልቅ ኀዘን ተውጦ ወደ መቃብሩ መጣ፤ መቃብሩም ዋሻ ነበረ፤ ድንጋይም ተገጥሞበት ነበር።
Explorează የዮሐንስ ወንጌል 11:38
7
የዮሐንስ ወንጌል 11:11
ይህንንም ከተናገረ በኋላ “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ፤” አላቸው።
Explorează የዮሐንስ ወንጌል 11:11
Acasă
Biblia
Planuri
Videoclipuri