1
ማቴዎስ 22:37-39
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
NASV
እርሱም እንዲህ አለው፤ “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ፤’ ይህ የመጀመሪያውና ከሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ ነው፤ ሁለተኛውም ያንኑ ይመስላል፤ ይህም፣ ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ’ የሚለው ነው፤
Compară
Explorează ማቴዎስ 22:37-39
2
ማቴዎስ 22:40
ሕግና ነቢያት በሙሉ በእነዚህ ሁለት ትእዛዞች ላይ የተንጠለጠሉ ናቸው።”
Explorează ማቴዎስ 22:40
3
ማቴዎስ 22:14
“የተጠሩት ብዙዎች፣ የተመረጡት ግን ጥቂቶች ናቸውና።”
Explorează ማቴዎስ 22:14
4
ማቴዎስ 22:30
ከትንሣኤ በኋላ ሰዎች እንደ ሰማይ መላእክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡም፤ አይጋቡም።
Explorează ማቴዎስ 22:30
5
ማቴዎስ 22:19-21
ለግብር የሚከፈለውን ገንዘብ እስኪ አሳዩኝ።” እነርሱም አንድ ዲናር አመጡለት። እርሱም፣ “በዚህ ገንዘብ ላይ የሚታየው መልክ የማን ነው? ጽሕፈቱስ የማን ነው?” አላቸው። እነርሱም፣ “የቄሳር ነው” አሉት። እርሱም መልሶ፣ “እንግዲያውስ የቄሳርን ለቄሳር፣ የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር ስጡ” አላቸው።
Explorează ማቴዎስ 22:19-21