1
ወደ ሮም ሰዎች 8:28
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
နှိုင်းယှဉ်
ወደ ሮም ሰዎች 8:28ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
2
ወደ ሮም ሰዎች 8:38-39
ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።
ወደ ሮም ሰዎች 8:38-39ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
3
ወደ ሮም ሰዎች 8:26
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤
ወደ ሮም ሰዎች 8:26ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
4
ወደ ሮም ሰዎች 8:31
እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?
ወደ ሮም ሰዎች 8:31ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
5
ወደ ሮም ሰዎች 8:1
እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።
ወደ ሮም ሰዎች 8:1ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
6
ወደ ሮም ሰዎች 8:6
ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
ወደ ሮም ሰዎች 8:6ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
7
ወደ ሮም ሰዎች 8:37
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
ወደ ሮም ሰዎች 8:37ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
8
ወደ ሮም ሰዎች 8:18
ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ።
ወደ ሮም ሰዎች 8:18ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
9
ወደ ሮም ሰዎች 8:35
ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?
ወደ ሮም ሰዎች 8:35ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
10
ወደ ሮም ሰዎች 8:27
ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና።
ወደ ሮም ሰዎች 8:27ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
11
ወደ ሮም ሰዎች 8:14
በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
ወደ ሮም ሰዎች 8:14ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
12
ወደ ሮም ሰዎች 8:5
እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ።
ወደ ሮም ሰዎች 8:5ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
13
ወደ ሮም ሰዎች 8:32
ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?
ወደ ሮም ሰዎች 8:32ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
14
ወደ ሮም ሰዎች 8:16-17
የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከብር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።
ወደ ሮም ሰዎች 8:16-17ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
15
ወደ ሮም ሰዎች 8:7
ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤
ወደ ሮም ሰዎች 8:7ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
16
ወደ ሮም ሰዎች 8:19
የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።
ወደ ሮም ሰዎች 8:19ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
17
ወደ ሮም ሰዎች 8:22
ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና።
ወደ ሮም ሰዎች 8:22ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
ပင်မစာမျက်နှာ
သမ္မာကျမ်းစာ
အစီအစဉ်များ
ဗီဒီယိုများ