1
ወደ ሮም ሰዎች 12:2
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
နှိုင်းယှဉ်
ወደ ሮም ሰዎች 12:2ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
2
ወደ ሮም ሰዎች 12:1
እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።
ወደ ሮም ሰዎች 12:1ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
3
ወደ ሮም ሰዎች 12:12
በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤
ወደ ሮም ሰዎች 12:12ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
4
ወደ ሮም ሰዎች 12:21
ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:21ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
5
ወደ ሮም ሰዎች 12:10
በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤
ወደ ሮም ሰዎች 12:10ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
6
ወደ ሮም ሰዎች 12:9
ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤
ወደ ሮም ሰዎች 12:9ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
7
ወደ ሮም ሰዎች 12:18
ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:18ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
8
ወደ ሮም ሰዎች 12:19
ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።
ወደ ሮም ሰዎች 12:19ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
9
ወደ ሮም ሰዎች 12:11
ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤
ወደ ሮም ሰዎች 12:11ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
10
ወደ ሮም ሰዎች 12:3
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:3ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
11
ወደ ሮም ሰዎች 12:17
ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:17ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
12
ወደ ሮም ሰዎች 12:16
እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:16ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
13
ወደ ሮም ሰዎች 12:20
ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።
ወደ ሮም ሰዎች 12:20ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
14
ወደ ሮም ሰዎች 12:14-15
የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:14-15ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
15
ወደ ሮም ሰዎች 12:13
ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:13ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
16
ወደ ሮም ሰዎች 12:4-5
በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።
ወደ ሮም ሰዎች 12:4-5ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
ပင်မစာမျက်နှာ
သမ္မာကျမ်းစာ
အစီအစဉ်များ
ဗီဒီယိုများ