1
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ ዓላማውም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
Palyginti
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:38-39
ይህንን ተረድቼአለሁ፤ ሞትም ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ገዢዎችም ቢሆኑ፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ጥልቀትም ቢሆን፥ ሌላ ፍጥረትም ቢሆን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:38-39
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:26
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ይረዳናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ያማልድልናል፤
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:26
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:31
እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:31
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:1
ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም።
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:1
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:6
ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:6
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37
በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37
8
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:18
የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ወደ ፊት ለእኛ ከሚገለጥልን ክብር ጋር ሲነጻጸር ምንም ዋጋ እንደሌለው እቆጥረዋለሁ።
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:18
9
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:35
ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው? መከራ ወይስ ሥቃይ፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ረሃብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ አደጋ፥ ወይስ ሰይፍ?
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:35
10
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:27
ልቦችንም የሚመረምረው እርሱ የመንፈስ ሐሳብ ምን እንደሆነ ያውቃል፥ ምክንያቱም መንፈስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ያማልዳልና።
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:27
11
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:14
በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ፥ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:14
12
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:5
እንደ ሥጋ የሚኖሩ አእምሮአቸው የሥጋን ነገር እንዲያስብ ያደርጋሉና፥ እንደ መንፈስ የሚኖሩ ግን አእምሮአቸው የመንፈስን ነገር እንዲያስብ ያደርጋሉ።
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:5
13
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:32
ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው እርሱ፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:32
14
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:16-17
የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈሱ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክርልናል። ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ከእርሱ ጋር የክብሩ ተካፋዮች እንድንሆን ከእርሱ ጋር መከራ ብንቀበል የእግዚአብሔር ወራሾችና ከክርስቶስም ጋር አብረን ወራሾች ነን።
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:16-17
15
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:7
ስለ ሥጋ ማሰብ የእግዚአብሔር ጠላት መሆን ነው፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም አይችልም፥
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:7
16
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:19
ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በታላቅ ናፍቆት ይጠባበቃልና።
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:19
17
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:22
እስከ አሁን ድረስ ፍጥረት ሁሉ አብሮ በመቃተትና በምጥ ሥቃይ እንደሚኖር እናውቃለንና።
Naršyti ወደ ሮሜ ሰዎች 8:22
Pradžia
Biblija
Planai
Vaizdo įrašai