1
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:58
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።
Palyginti
Naršyti 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:58
2
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:57
ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ድልን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።
Naršyti 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:57
3
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:33
አትሳቱ፤ “መጥፎ ጓደኝነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።”
Naršyti 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:33
4
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:10
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን የሆንሁትን ሆኛለሁ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋ ከንቱ አልሆነም፤ ይልቁን ከሁሉም በላይ በትጋት ሠርቻለሁ፤ ሆኖም ግን እኔ ሳልሆን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው።
Naršyti 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:10
5
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:55-56
“ሞት ሆይ፤ ድል መንሣትህ የት አለ? ሞት ሆይ፤ መውጊያህስ የት አለ?”። የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው፤ የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው።
Naršyti 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:55-56
6
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:51-52
እነሆ፥ አንድ ምስጢር እነግራችኋለሁ! ሁላችን አናንቀላፋም፤ ነገር ግን ሁላችንም እንለወጣለን፤ የመጨረሻው መለከት ሲነፋ፥ ድንገት፥ በቅጽበተ ዐይን፥ መለከት ይነፋል፤ ሙታን የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን።
Naršyti 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:51-52
7
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:21-22
ሞት በአንድ ሰው በኩል እንደመጣ፥ የሙታንም ትንሣኤ በአንድ ሰው በኩል ሆኖአልና። ሰዎች ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፥ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤
Naršyti 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:21-22
8
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:53
የሚጠፋው የማይጠፋውን፥ የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና።
Naršyti 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:53
9
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:25-26
ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ ሥር እስከሚያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና። የሚደመሰሰው የመጨረሻው ጠላት ሞት ነው፤
Naršyti 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:25-26
Pradžia
Biblija
Planai
Vaizdo įrašai