1
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:17-18
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና። እንደዚህ አድርጎ ክርስቶስን የሚያገልግል እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል፤ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው።
比較
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:17-18で検索
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:8
በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:8で検索
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:19
እንግዲህ የሰላም ነገርና እርስ በርሳችንም የምንታነጽበትን ነገር እንከተል።
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:19で検索
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:13
እንግዲህ ከዚህ በኋላ አንዳችን በአንዳችን ላይ አንፍረድ፤ ነገር ግን ከመፍረድ ይልቅ ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖርበት ይወስን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:13で検索
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:11-12
“እኔ ሕያው ነኝ፤” ይላል ጌታ፤ “ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ልሳንም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል፤” ተብሎ ተጽፎአልና። እንግዲያስ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:11-12で検索
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:1
በእምነት የደከመውንም አከራካሪ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሳትፈርዱበት ተቀበሉት።
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:1で検索
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:4
አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን ጌታ ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:4で検索
ホーム
聖書
読書プラン
ビデオ