1
የዮሐንስ ወንጌል 13:34-35
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እርሱም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። እርስ በርሳችሁ ብትዋድዱ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።”
比較
የዮሐንስ ወንጌል 13:34-35で検索
2
የዮሐንስ ወንጌል 13:14-15
እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ልትተጣጠቡ ይገባል። እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተም እንዲሁ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።
የዮሐንስ ወንጌል 13:14-15で検索
3
የዮሐንስ ወንጌል 13:7
ኢየሱስም መልሶ “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፤ በኋላ ግን ታስተውላለህ” አለው።
የዮሐንስ ወንጌል 13:7で検索
4
የዮሐንስ ወንጌል 13:16
እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም፤ መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም፤
የዮሐንስ ወንጌል 13:16で検索
5
የዮሐንስ ወንጌል 13:17
ይህንን ስታውቁና ስታደርጉ ብፁዓን ናችሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 13:17で検索
6
የዮሐንስ ወንጌል 13:4-5
ከማእድ ተነሣ፤ ልብሱንም አኖረ፤ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውሃ ጨመረ፤ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ማጠብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ማበስ ጀመረ።
የዮሐንስ ወንጌል 13:4-5で検索
ホーム
聖書
読書プラン
ビデオ