1
የማቴዎስ ወንጌል 24:12-13
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ከሕገ ወጥነት ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻው የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
Bandingkan
Telusuri የማቴዎስ ወንጌል 24:12-13
2
የማቴዎስ ወንጌል 24:14
ለሕዝቦች ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥቱ ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፤ በዚያን ጊዜ መጨረሻው ይመጣል።
Telusuri የማቴዎስ ወንጌል 24:14
3
የማቴዎስ ወንጌል 24:6
ጦርነትንና የጦርነትን ወሬ ትሰማላችሁ፤ አስተውሉ፥ አትደንግጡ፥ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፤ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው።
Telusuri የማቴዎስ ወንጌል 24:6
4
የማቴዎስ ወንጌል 24:7-8
ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ ራብና የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህ ሁሉ የምጥ መጀመሪያ ናቸው።
Telusuri የማቴዎስ ወንጌል 24:7-8
5
የማቴዎስ ወንጌል 24:35
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።
Telusuri የማቴዎስ ወንጌል 24:35
6
የማቴዎስ ወንጌል 24:5
ብዙዎች ‘መሢሑ እኔ ነኝ’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና ብዙዎችንም ያስታሉ።
Telusuri የማቴዎስ ወንጌል 24:5
7
የማቴዎስ ወንጌል 24:9-11
“በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ይገድሉአችኋልም፤ ስለ ስሜም በሕዝቦች ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። በዚያን ጊዜ ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም ይጠላላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፤
Telusuri የማቴዎስ ወንጌል 24:9-11
8
የማቴዎስ ወንጌል 24:4
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
Telusuri የማቴዎስ ወንጌል 24:4
9
የማቴዎስ ወንጌል 24:44
ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።
Telusuri የማቴዎስ ወንጌል 24:44
10
የማቴዎስ ወንጌል 24:42
እንግዲህ ጌታችሁ በየትኛው ቀን እንደሚመጣ አታውቁምና ነቅታችሁ ጠብቁ።
Telusuri የማቴዎስ ወንጌል 24:42
11
የማቴዎስ ወንጌል 24:36
“ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአብ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ፥ ወልድም ቢሆን፥ ማንም የሚያውቅ የለም።
Telusuri የማቴዎስ ወንጌል 24:36
12
የማቴዎስ ወንጌል 24:24
ሐሰተኞች መሲሖችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፤ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ለማሳት ታላላቅ ምልክትንና ድንቅ ነገሮችን ያሳያሉ።
Telusuri የማቴዎስ ወንጌል 24:24
13
የማቴዎስ ወንጌል 24:37-39
በኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣትም እንዲሁ ይሆናልና። ከጥፋት ውሃ በፊት በነበሩት ከእነዚያ ቀናት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡ እንደ ነበሩና፥ የጥፋት ውሃ መጥቶ ሁሉን እስኪወስድ ድረስ እንዳላወቁት፥ የሰው ልጅ መምጣትም ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።
Telusuri የማቴዎስ ወንጌል 24:37-39
Beranda
Alkitab
Rencana
Video