1
የሉቃስ ወንጌል 5:4
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ንግግሩንም ከጨረሰ በኋላ፥ ስምዖንን፦ “ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል፤ መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ፤” አለው።
Comparer
Explorer የሉቃስ ወንጌል 5:4
2
የሉቃስ ወንጌል 5:5-6
ስምዖንም መልሶ፦ “አቤቱ! ሌሊቱን ሙሉ ብንደክምም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ፤” አለው። ይህንም ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፤ መረቦቻቸውም ተቀደዱ።
Explorer የሉቃስ ወንጌል 5:5-6
3
የሉቃስ ወንጌል 5:16
እርሱ ግን ገለል ብሎ ወደ በምድረ በዳዎች እየሄደ ይጸልይ ነበር።
Explorer የሉቃስ ወንጌል 5:16
4
የሉቃስ ወንጌል 5:32
ኀጢአተኞችን ወደ ንስሓ ልጠራ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም።”
Explorer የሉቃስ ወንጌል 5:32
5
የሉቃስ ወንጌል 5:8
ስምዖን ጴጥሮስም ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጉልበት ፊት ወድቆ፦ “ጌታ ሆይ! እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና ከኔ ራቅ፤” አለው።
Explorer የሉቃስ ወንጌል 5:8
6
የሉቃስ ወንጌል 5:31
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም፤
Explorer የሉቃስ ወንጌል 5:31
7
የሉቃስ ወንጌል 5:11
ታንኳዎቹንም ወደ ምድር አድርሰው ሁሉን ትተው ተከተሉት።
Explorer የሉቃስ ወንጌል 5:11
8
የሉቃስ ወንጌል 5:12-13
ከከተማዎችም በአንዲቱ ሳለ፥ እነሆ፥ ለምጽ የወረሰው አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስንም ባየው ጊዜ በግንባሩ ተደፍቶ፦ “ጌታ ሆይ! ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ፤” ሲል ተማጸነው። እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ “እፈቅዳለሁ፤ ንጻ፤” አለው፤ ወዲያውም ለምጹ ለቀቀው።
Explorer የሉቃስ ወንጌል 5:12-13
9
የሉቃስ ወንጌል 5:15
ስለ እርሱ የሚባለው ግን ይበልጡን በስፋት ተሰራጨ፤ ብዙ ሕዝብም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ይሰበሰቡ ነበር፤
Explorer የሉቃስ ወንጌል 5:15
Accueil
Bible
Plans
Vidéos