1
የሉቃስ ወንጌል 14:26
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
“ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት እንኳን ሳይቀር ካልናቀ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
Comparer
Explorer የሉቃስ ወንጌል 14:26
2
የሉቃስ ወንጌል 14:27
ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
Explorer የሉቃስ ወንጌል 14:27
3
የሉቃስ ወንጌል 14:11
ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል።”
Explorer የሉቃስ ወንጌል 14:11
4
የሉቃስ ወንጌል 14:33
እንግዲህ እንደዚሁ ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ማንም ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
Explorer የሉቃስ ወንጌል 14:33
5
የሉቃስ ወንጌል 14:28-30
ከእናንተ ግንብ ሊሠራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ እንዳለው አስቀድሞ ተቀምጦ ወጪውን የማይቈጥር ማን ነው? ያለዚያ መሠረቱን ቢያኖር፥ ሊደመድመውም ቢያቅተው፥ ያዩት ሁሉ ‘ይህ ሰው ሊሠራ ጀምሮ መደምደም አቃተው፤’ ብለው ሊቀልዱበት ይጀምራሉ።
Explorer የሉቃስ ወንጌል 14:28-30
6
የሉቃስ ወንጌል 14:13-14
ነገር ግን ግብዣ ባሰናዳህ ጊዜ ድሆችንና ጉንድሾችን አንካሶችንም ዐይነ ስውሮችንም ጥራ፤ የሚመልሱት አጸፋ የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና።”
Explorer የሉቃስ ወንጌል 14:13-14
7
የሉቃስ ወንጌል 14:34-35
“ጨው መልካም ነው፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ለምድርም ሆነ ለፍግ መቈለያ አይጠቅምም፤ ወደ ውጭም ይጥሉታል። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”
Explorer የሉቃስ ወንጌል 14:34-35
Accueil
Bible
Plans
Vidéos