1
የሐዋርያት ሥራ 2:38
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ ኃጢአታችሁም ይቅር እንዲባልላችሁ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የእግዚአብሔር ስጦታ የሆነውን መንፈስ ቅዱስንም ትቀበላላችሁ፤
Comparer
Explorer የሐዋርያት ሥራ 2:38
2
የሐዋርያት ሥራ 2:42
እነርሱም የሐዋርያትን ትምህርት በመስማት፥ በኅብረት በመኖር፥ ማዕድን አብሮ በመብላትና በጸሎት ይተጉ ነበር።
Explorer የሐዋርያት ሥራ 2:42
3
የሐዋርያት ሥራ 2:4
ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ መንፈስ ቅዱስ እንዲናገሩ በሰጣቸው ችሎታ መጠን በሌሎች ቋንቋዎች መናገር ጀመሩ።
Explorer የሐዋርያት ሥራ 2:4
4
የሐዋርያት ሥራ 2:2-4
በድንገት ብርቱ ዐውሎ ነፋስ የመሰለ ድምፅ ከሰማይ መጣ፤ የነበሩበትንም ቤት ሞላው። የእሳት ነበልባሎች የሚመስሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ ተከፋፍለውም በእያንዳንዳቸው ላይ ዐረፉባቸው። ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ መንፈስ ቅዱስ እንዲናገሩ በሰጣቸው ችሎታ መጠን በሌሎች ቋንቋዎች መናገር ጀመሩ።
Explorer የሐዋርያት ሥራ 2:2-4
5
የሐዋርያት ሥራ 2:46-47
በየቀኑ በቤተ መቅደስ በአንድነት ይሰበሰቡ ነበር፤ በቤታቸውም እንጀራ እየቈረሱ በደስታና በጥሩ ልብ ይመገቡ ነበር፤ ጌታንም ያመሰግኑ ነበር፤ ሰውም ሁሉ ያከብራቸው ነበር፤ እግዚአብሔርም የሚድኑትን ሰዎች በየቀኑ ወደ ማኅበራቸው ይጨምር ነበር።
Explorer የሐዋርያት ሥራ 2:46-47
6
የሐዋርያት ሥራ 2:17
‘እግዚአብሔር በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል ይላል፤ መንፈሴን በሰው ሁሉ ላይ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ፤ ጐልማሶቻችሁም ራእይ ያያሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ።
Explorer የሐዋርያት ሥራ 2:17
7
የሐዋርያት ሥራ 2:44-45
አማኞች ሁሉ በአንድነት አብረው ይኖሩ ነበር፤ ያላቸውም ነገር ሁሉ የጋራ ነበር። ዕርሻቸውንና ሀብታቸውን እየሸጡ ገንዘቡን ለእያንዳንዱ እንደሚያስፈልገው ያከፋፍሉ ነበር።
Explorer የሐዋርያት ሥራ 2:44-45
8
የሐዋርያት ሥራ 2:21
የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።’
Explorer የሐዋርያት ሥራ 2:21
9
የሐዋርያት ሥራ 2:20
ታላቁና አስገራሚው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት፥ ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ደም ትመስላለች።
Explorer የሐዋርያት ሥራ 2:20
Accueil
Bible
Plans
Vidéos