1
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:2
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
ይህን ዓለም አትምሰሉ፤ ልባችሁንም አድሱ፤ እግዚአብሔር የሚወደውን መልካሙንና እውነቱን፥ ፍጹሙንም መርምሩ።
Porovnat
Zkoumat ወደ ሮሜ ሰዎች 12:2
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:1
ወንድሞቻችን፥ ሰውነታችሁን ለእግዚአብሔር ሕያውና ቅዱስ፥ ደስ የሚያሰኝም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እማልዳችኋለሁ። ይህም በዕውቀት የሚሆን አገልግሎታችሁ ነው።
Zkoumat ወደ ሮሜ ሰዎች 12:1
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:12
በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ ለጸሎት ትጉ።
Zkoumat ወደ ሮሜ ሰዎች 12:12
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:21
ክፉውን በመልካም ሥራ ድል ንሣው እንጂ ክፉውን በክፉ ድል አትንሣው።
Zkoumat ወደ ሮሜ ሰዎች 12:21
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:10
እርስ በርሳችሁ በወንድማማችነት መዋደድ ተዋደዱ፤ የምትራሩም ሁኑ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤ መምህሮቻችሁንም አክብሩ።
Zkoumat ወደ ሮሜ ሰዎች 12:10
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:9
ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን፤ ከክፉ ራቁ፤ በጎውንም ያዙ፤ ለጽድቅ አድሉ፤
Zkoumat ወደ ሮሜ ሰዎች 12:9
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:18
ቢቻላችሁስ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።
Zkoumat ወደ ሮሜ ሰዎች 12:18
8
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:19
ወንድሞቻችን፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ቍጣን አሳልፏት፥ “እኔ እበቀላለሁ፤ እኔ ብድራትን እከፍላለሁ ይላል እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአልና።
Zkoumat ወደ ሮሜ ሰዎች 12:19
9
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:11
ለሥራ ከመትጋት አትስነፉ፤ በመንፈስ ሕያዋን ሁኑ፤ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤
Zkoumat ወደ ሮሜ ሰዎች 12:11
10
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:3
በተሰጠኝ በእግዚአብሔር ጸጋ ሁላችሁም እንዳትታበዩ እነግራችኋለሁ፤ ራሳችሁን ከዝሙት የምታነጹበትን ዐስቡ እንጂ ትዕቢትን አታስቡ፤ ሁሉም እንደ እምነቱ መጠን እግዚአብሔር እንደ አደለው ይኑር።
Zkoumat ወደ ሮሜ ሰዎች 12:3
11
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:17
ክፉ ላደረገባችሁም ክፉ አትመልሱለት፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎውን ተነጋገሩ።
Zkoumat ወደ ሮሜ ሰዎች 12:17
12
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:16
እርስ በርሳችሁም በአንድ ዐሳብ ተስማሙ፤ ትዕቢትን ግን አታስቡ፤ ራሱን የሚያዋርደውንም ሰው ምሰሉ፤ እና ዐዋቆች ነን አትበሉ።
Zkoumat ወደ ሮሜ ሰዎች 12:16
13
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:20
ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ ቢጠማም አጠጣው፤ ይህን ብታደርግ የእሳት ፍሕም በራሱ ላይ ትከምራለህ።
Zkoumat ወደ ሮሜ ሰዎች 12:20
14
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:14-15
የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚለው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሰው ጋርም አልቅሱ።
Zkoumat ወደ ሮሜ ሰዎች 12:14-15
15
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:13
በችግራቸው ቅዱሳንን ለመርዳት ተባበሩ፤ እንግዳ መቀበልንም አዘውትሩ።
Zkoumat ወደ ሮሜ ሰዎች 12:13
16
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:4-5
በአንዱ ሰውነታችን ብዙ የአካል ክፍሎች እንዳሉ፥ ሥራቸውም ልዩ ልዩ እንደ ሆነ፥ እንዲሁ ሁላችን ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፤ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው አካሎች ነን፤ ስጦታውም ልዩ ልዩ ነው፤
Zkoumat ወደ ሮሜ ሰዎች 12:4-5
Domů
Bible
Plány
Videa