1
ወደ ገላትያ ሰዎች 6:9
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
መልካምን ሥራ ለመሥራት አንታክት፥ ካልዛልን ወቅቱ በደረሰ ጊዜ እናጭዳለንና።
Porovnat
Zkoumat ወደ ገላትያ ሰዎች 6:9
2
ወደ ገላትያ ሰዎች 6:10
ስለዚህ ጊዜ ሳለን ለሰው ሁሉ፥ በተለይም ለእምነት ቤተሰቦች መልካም እናድርግ።
Zkoumat ወደ ገላትያ ሰዎች 6:10
3
ወደ ገላትያ ሰዎች 6:2
የእርስ በርሳችሁን ሸክም ተሸከሙ፥ በዚህም የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ።
Zkoumat ወደ ገላትያ ሰዎች 6:2
4
ወደ ገላትያ ሰዎች 6:7
አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም፤ ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳልና።
Zkoumat ወደ ገላትያ ሰዎች 6:7
5
ወደ ገላትያ ሰዎች 6:8
ምክንያቱም ወደ ገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ ጥፋትን ያጭዳል፥ በመንፈስ የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘለዓለምን ሕይወት ያጭዳል።
Zkoumat ወደ ገላትያ ሰዎች 6:8
6
ወደ ገላትያ ሰዎች 6:1
ወንድሞች ሆይ! ሰው ማንኛውንም ኃጢአት አድርጎ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ዓይነቱን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተም እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።
Zkoumat ወደ ገላትያ ሰዎች 6:1
7
ወደ ገላትያ ሰዎች 6:3-5
አንድ ሰው ምንም ሳይሆን አንድ ነገር የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላልና። እያንዳንዱ የገዛ ሥራውን ይፈትን፤ ከዚያም በኋላ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል፥ ስለ ሌላው ግን አይደለም። እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ይሸከማልና።
Zkoumat ወደ ገላትያ ሰዎች 6:3-5
Domů
Bible
Plány
Videa