1
ኦሪት ዘጸአት 2:24-25
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ጭንቀት የተሞላበትን ጩኸታቸውንም ሰምቶ እግዚአብሔር ከአብርሃም፥ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን አስታወሰ። እግዚአብሔር እስራኤላውያን በባርነት መጨነቃቸውን አይቶ ስለ እነርሱ አሰበ።
Porovnat
Zkoumat ኦሪት ዘጸአት 2:24-25
2
ኦሪት ዘጸአት 2:23
ከብዙ ዓመቶች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ እስራኤላውያን ግን አሁንም በባርነት ቀንበር ሥር በመጨነቅ ርዳታ ለማግኘት በመጮኽ ላይ ነበሩ፤ ጩኸታቸውም ወደ እግዚአብሔር ደረሰ።
Zkoumat ኦሪት ዘጸአት 2:23
3
ኦሪት ዘጸአት 2:10
ሕፃኑም ባደገ ጊዜ ወደ ንጉሡ ልጅ አመጣችው፤ የእርስዋም ልጅ ተባለ። እርስዋም “ከውሃ ያወጣሁት ስለ ሆነ ስሙ ሙሴ ተብሎ ይጠራ” አለች።
Zkoumat ኦሪት ዘጸአት 2:10
4
ኦሪት ዘጸአት 2:9
የንጉሡ ልጅም ሴትዮይቱን “ይህን ሕፃን ወስደሽ እያጠባሽ አሳድጊልኝ፤ ደመወዝሽንም እከፍልሻለሁ” አለቻት፤ ስለዚህ ሴቲቱ ሕፃኑን ወስዳ ታጠባው ጀመር።
Zkoumat ኦሪት ዘጸአት 2:9
5
ኦሪት ዘጸአት 2:5
በዚህ ጊዜ የንጉሡ ሴት ልጅ ልትታጠብ ወደ ወንዝ ወረደች፤ ሴቶች አገልጋዮችዋም በወንዙ ዳር ይሄዱ ነበር፤ እርስዋም በቀጤማ መካከል የተቀመጠ አንድ ቅርጫት አየች፤ አገልጋይዋንም ልካ አስመጣችው።
Zkoumat ኦሪት ዘጸአት 2:5
6
ኦሪት ዘጸአት 2:11-12
ሙሴ ባደገ ጊዜ ወገኖቹን ለመጐብኘት ሄደ፤ ከባድ ሥራ መሥራታቸውን ተመለከተ፤ እንዲያውም አንድ ግብጻዊ ከወገኖቹ አንዱ የሆነውን ዕብራዊ ሲደበድብ አየ። ሙሴ ዙሪያውን ተመልክቶ ማንም እንደማያየው ከተረዳ በኋላ ግብጻዊውን ገድሎ በአሸዋ ውስጥ ደበቀው።
Zkoumat ኦሪት ዘጸአት 2:11-12
Domů
Bible
Plány
Videa