1
ኦሪት ዘፍጥረት 37:5
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
ዮሴፍም ሕልምን አለመ፤ ለወንድሞቹም ነገራቸው።
Параўнаць
Даследуйце ኦሪት ዘፍጥረት 37:5
2
ኦሪት ዘፍጥረት 37:3
ያዕቆብም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወድደው ነበር፤ እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበርና። በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት።
Даследуйце ኦሪት ዘፍጥረት 37:3
3
ኦሪት ዘፍጥረት 37:4
ወንድሞቹም አባታቸው ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ እንደሚወድደው በአዩ ጊዜ ጠሉት፤ በሰላም ይናገሩትም ዘንድ አልቻሉም።
Даследуйце ኦሪት ዘፍጥረት 37:4
4
ኦሪት ዘፍጥረት 37:9
ደግሞም ሌላ ሕልምን አየ፤ ለአባቱና ለወንድሞቹም ነገራቸው፤ እንዲህም አለ፥ “እነሆ፥ ደግሞ ሌላ ሕልም አለምሁ፤ ሕልሙም እንዲህ ነው፦ ፀሐይና ጨረቃ ዐሥራ አንድ ከዋክብትም ይሰግዱልኝ ነበር።”
Даследуйце ኦሪት ዘፍጥረት 37:9
5
ኦሪት ዘፍጥረት 37:11
ወንድሞቹም ቀኑበት፤ አባቱ ግን ይህን ነገር በልቡ ይጠብቀው ነበር።
Даследуйце ኦሪት ዘፍጥረት 37:11
6
ኦሪት ዘፍጥረት 37:6-7
እርሱም አላቸው፥ “እኔ ያለምሁትን ሕልም ስሙ፤ እነሆ፥ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበርና፥ እነሆ፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶዎች በዙርያ ከብበው እነሆ፥ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”
Даследуйце ኦሪት ዘፍጥረት 37:6-7
7
ኦሪት ዘፍጥረት 37:20
ኑ፥ እንግደለውና በአንድ ጕድጓድ ውስጥ እንጣለው፤ ክፉ አውሬም በላው እንላለን፤ ሕልሞቹም ምን እንደሚሆኑ እናያለን።”
Даследуйце ኦሪት ዘፍጥረት 37:20
8
ኦሪት ዘፍጥረት 37:28
እነዚያ ይስማኤላውያን ነጋዴዎችም ሲያልፉ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ ጐትተው አወጡት፤ ለይስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።
Даследуйце ኦሪት ዘፍጥረት 37:28
9
ኦሪት ዘፍጥረት 37:19
አንዱም ለአንዱ እንዲህ አለው፥ “ያ ባለ ሕልም ይኸው መጣ።
Даследуйце ኦሪት ዘፍጥረት 37:19
10
ኦሪት ዘፍጥረት 37:18
እነርሱም ወደ እነርሱ ሳይቀርብ ከሩቅ አስቀድመው አዩት፥ ይገድሉትም ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ።
Даследуйце ኦሪት ዘፍጥረት 37:18
11
ኦሪት ዘፍጥረት 37:22
ሮቤልም፥ “ደም አታፍስሱ፤ በዚች ምድረ በዳ ባለችው ጕድጓድ ጣሉት፤ ነገር ግን እጃችሁን አትጣሉበት” አላቸው። ሮቤልም እንዲህ ማለቱ ከእጃቸው ሊያድነውና ወደ አባቱ ሊመልሰው ነው።
Даследуйце ኦሪት ዘፍጥረት 37:22
Стужка
Біблія
Планы чытання
Відэа