1
የዮሐንስ ወንጌል 16:33
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ፤”
Параўнаць
Даследуйце የዮሐንስ ወንጌል 16:33
2
የዮሐንስ ወንጌል 16:13
የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ግን እርሱ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ ከራሱ አይናገርምና፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።
Даследуйце የዮሐንስ ወንጌል 16:13
3
የዮሐንስ ወንጌል 16:24
እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ፤ ትቀበሉማላችሁ።”
Даследуйце የዮሐንስ ወንጌል 16:24
4
የዮሐንስ ወንጌል 16:7-8
እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ ብሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤
Даследуйце የዮሐንስ ወንጌል 16:7-8
5
የዮሐንስ ወንጌል 16:22-23
እንግዲህ እናንተ ደግሞ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እንደገና አያችኋለሁ፤ ልባችሁም ደስ ይለዋል፤ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም። በዚያን ቀንም ከእኔ ምንም ነገር አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።
Даследуйце የዮሐንስ ወንጌል 16:22-23
6
የዮሐንስ ወንጌል 16:20
እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ታለቅሳለችሁ፤ ሙሾም ታወጣላችሁ፤ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተም ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።
Даследуйце የዮሐንስ ወንጌል 16:20
Стужка
Біблія
Планы чытання
Відэа