የፍለጋ ውጤቶች ለ፦ praise
1 ተሰሎንቄ 5:18 (NASV)
በማናቸውም ሁኔታ አመስግኑ፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ይህ ነውና።
መዝሙር 139:14 (NASV)
ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፤ ነፍሴም ይህን በውል ተረድታለች።
መዝሙር 63:3 (NASV)
ምሕረትህ ከሕይወት ይበልጣልና፤ ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።
መዝሙር 63:4 (NASV)
እንግዲህ፣ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፤ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ።
መዝሙር 100:4 (NASV)
በምስጋና ወደ ደጆቹ፣ በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም ባርኩ፤
ዕብራውያን 13:15 (NASV)
ስለዚህ ዘወትር የምስጋናን መሥዋዕት፣ ይኸውም ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ በኢየሱስ አማካይነት ለእግዚአብሔር እናቅርብ።
ፊልጵስዩስ 4:4 (NASV)
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ!
ፊልጵስዩስ 4:8 (NASV)
በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፤ እውነት የሆነውን ሁሉ፣ ክቡር የሆነውን ሁሉ፣ ትክክል የሆነውን ሁሉ፣ ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፣ ተወዳጅ የሆነውን ሁሉ፣ መልካም የሆነውን ሁሉ፣ በጎነት ቢሆን ወይም ምስጋና እንደ እነዚህ ስላሉት ነገሮች አስቡ።
ቈላስይስ 3:16 (NASV)
የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁ በጥበብ ሁሉ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በማሕሌት፣ በመንፈሳዊም ቅኔ በማመስገን በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።
1 ተሰሎንቄ 5:16 (NASV)
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤
1 ተሰሎንቄ 5:17 (NASV)
ሳታቋርጡ ጸልዩ፤
መዝሙር 9:1 (NASV)
እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ስለ ድንቅ ሥራዎችህም ሁሉ እናገራለሁ።
መዝሙር 34:1 (NASV)
እግዚአብሔር ን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፤ ምስጋናውም ዘወትር ከአፌ አይለይም።
መዝሙር 100:1 (NASV)
ምድር ሁሉ ለ እግዚአብሔር እልል በሉ፤
መዝሙር 100:2 (NASV)
እግዚአብሔር ን በደስታ አገልግሉት፤ በፍሥሓ ዝማሬ ፊቱ ቅረቡ።
መዝሙር 100:3 (NASV)
እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤ እርሱ ፈጠረን፤ እኛም የርሱ ነን ፤ እኛ ሕዝቡ የማሰማሪያው በጎች ነን።
መዝሙር 100:5 (NASV)
እግዚአብሔር ቸር፣ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፤ ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።
መዝሙር 103:1 (NASV)
ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔር ን ባርኪ፤ የውስጥ ሰውነቴም ሁሉ ቅዱስ ስሙን ባርኪ።
መዝሙር 103:2 (NASV)
ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔር ን ባርኪ፤ ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፤
መዝሙር 150:6 (NASV)
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። ሃሌ ሉያ።
1 ዜና መዋዕል 29:11 (NASV)
እግዚአብሔር ሆይ፤ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና፤ ታላቅነት፣ ኀይል፣ ክብርና ግርማ የአንተ ነው። እግዚአብሔር ሆይ፤ መንግሥትም የአንተ ነው፤ አንተም እንደ ራስ ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያልህ ነህ።
መዝሙር 42:11 (NASV)
ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፣ አዳኜና አምላኬን ገና አመሰግነዋለሁና።
መዝሙር 63:5 (NASV)
ነፍሴ በቅቤና በሥብ እንደሚረካ ሰው ትረካለች፤ አፌም በሚያዜሙ ከንፈሮች በደስታ ያወድስሃል።
መዝሙር 95:2 (NASV)
ምስጋና ይዘን ፊቱ እንቅረብ፤ በዝማሬም እናወድሰው።
መዝሙር 103:3 (NASV)
ኀጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፣ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፣