1ኛ ጴጥሮስ: የ5 ቀናት የንባብ ዕቅድናሙና

ጴጥሮስ ደብዳቤውን ሲጀምር የምስራችን በመናገር ነው፡፡ የሆነ ጊዜ ላይ ከእግዚአብሔር ህዝብ ውጪ የሆኑት አህዛብ ተደራሲያን አሁን ግን በእግዚአብሔር ተመርጠዋል፡፡ እኚህ መፃተኞች በክርስቶስ የተገኙና ዳግም በመወለድ የእግዚአብሔር ቤተሰብ የሆኑ ናቸው፡፡ ነገር ግን በኢየሱስና በመከራው የተረጋገጠው ይህ ደህንነት አሁንም ድረስ በምድር ምሉዕ አይደለም፡፡ ለአሁኑ የእግዚአብሔር ምርጦቹ የሆኑት ህዝቡ በመፃተኝነት መጠበቅ የግድ ይላቸዋል፡፡ ስለዚህ ጴጥሮስ ለህዝቡ መዘጋጀት እንዳለባቸው ይናገራል፡፡
ልክ እስራኤል ግብፅን ለቀው ወደ ተስፋይቱ ምድር ሊገቡ ሲሉ እንደተዘጋጁት ሁሉ እኚህም አማኞች ወደ አዲሲቷ ምድር ተጓዦች እንደመሆናቸው ወገባቸውን መታጠቅ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ለጴጥሮስ ይህ ማለት ያንኑ ዓይነት ባህሪ ማንፀባረቅና ኢየሱስን ማዕከል ያደረገ ተስፋ መያዝ ማለት ነው። የእግዚአብሔር ሰዎች የአሮጌውን መንግስት መሻትና ምርጫ አሽቀንጥረው በመጣል የእግዚአብሔር መንግሥት የሚፈልገውን ዓይነት ቅድስናን ለብሰዋል። መዘጋጀት ማለት ደግሞ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ኢየሱስ በሚያሳልፈው የምሥራች ሁሉ ላይ ሙሉ በሙሉ ተስፋ ያደርጋሉ ማለት ነው። ንጉሱ ኢየሱስን መታመንም ቢሆን እንደ እግዚአብሔር መንግስት ዜጋ መኖር ሁለቱም ወደ አዲሲቷ ሀገር እንዴት ለመግባት እንደተዘጋጀን የሚያሳዩ ናቸው፡፡
ነገር ግን የሌላ ሀገር ዜጋ ኑሮ የፍርሃት ኑሮም ጭምር ነው፡፡ ፍርሃቱ የመሰቃየት ወይም ልዩ የመሆናቸው ብቻ አይደለም (ምንም ያ እንኳን እውነታ ቢሆንም)፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ዜግነት ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍልም የማወቅ ፍርሃት ነው። የእግዚአብሔር ህዝቦች ርካሽ በሆኑ እንደ ወርቅና ብር ዓይነት ነገሮች ሳይሆን ትድግና የሆነላቸው፤ ነገር ግን ውድ በሆነው በከበረው በኢየሱስ ደም ነው፡፡ እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት የወጡት ደም በተቀባው የበር መቃን ስር ካለፉ በኋላ ነው፡፡ አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ወደ አዲሱ ቤታቸው ሲጓዙ በደም መስቀል ጥላ ሥር ማለፍ የግድ ይላቸዋል፡፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች እንደ አዳኛቸው መሥዋዕታዊ ፍቅር እንዲኖራቸው ተጠርተዋል፤ እንዲሁም ኢየሱስን በመስቀል ላይ የቸነከረውን ዓይነት ክፋትን ያስወግዱ ዘንድ ተጠርተዋል። አማኞች ሁሉ አሮጌ የሆነውን ባህሪ በመተው ስላደረገላቸው ነገር እግዚአብሔርን ላለማሳዘን ባለ ፍርሃት ሆነው ሌላኛውን ተስፋ ትኩረት ማድረግ አለባቸው፡፡
እግዚአብሔር ህዝቡን ለመታደግ እርሱ እንደሚሞት ከዘላለም ዓለም በፊት ያውቀዋል፡፡ በኢየሱስ የዘላለምን ዕቅድ እንዲሁም ስለራሱ ህዝብ ሲል ሰውነቱን እንደሚሰዋ መወሰኑን እናውቃለን፡፡ ያ ተስፋችን ነው፡፡ ለዚያም ነው የምንፈራው፡፡ ለዚያም ነው ምፃቱን ስንጠባበቅ እንደ እግዚአብሔር መንግስት ዜጎች መኖር የተገባን፡፡
እንደ ሌላ ሀገር ዜጋ ሆኖ መቆየት በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ ስለ ኢየሱስ ባላችሁ ታማኝነት ምክንያት መገለልና መሰደድ ከዚያም ያለፈ ነገር ይገጥማችኋል፡፡ ጴጥሮስ ቀጥሎም ዳግም የተወለድነው ከማይተፋውና ዕድፈት በሌለበት በእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ያክላል፡፡ በእርሱ ዘመን እጅግ ኃያል የነበረችውን ባቢሎንን የእግዚአብሔር ቃል ፈፅሞ እንደሚያጠፋት የተናገረውን የነቢዩ ኢሳይያስን ንግግር ማጣቀሻ አድርጎ ተናግሯል፡፡ በኢየሱስ ይህ ቃል አለው፡፡ እግዚአብሔርን ባቢሎንም ሆነ ሮም ቃሉን ከመጠበቅ አያስቆሙትም፡፡ ከዘላለም ዓለም በፊት ስጋ በለበሰው፤ ቃል ንጉስ በሆነው በልጁ በኩል ሰዎችን ሁሉ ለማዳን መርጧል፡፡
ማንም ሀገር እግዚአብሔርን አያስቆመውም፡፡ የኢየሱስ ትንሣኤ እኛን ሞት ወደ ተገደለበት መንግሥት ዳግም መልሶናል። በእግዚአብሔር ቃልና በልጁ ምክንያት ዕድፈት የሌለብንና የማንጠፋ ነን፡፡ በዘላለማዊው መንግሥት ውስጥ ተካታች የመሆናችን ተስፋ መንግስቱ እንደመጣ ዓይነት ኑሮ እንድንመላለስሊያነሳሳን ይገባል።
በምሳሌያዊ አነጋገር ለአይነተኛ ለውጥ ሕፃናት ወተትን እንደሚሹ ዓይነት ኑሮን እንድንለማመድ ጴጥሮስ ይነግረናል፡፡ ወተት ልጅን የሚያሳድግ ነው፡፡ ጴጥሮስ የእግዚአብሔም ልጆች ወደ ዜግነታቸው የሚያድጉት ኢየሱስ የሰራልንን የምስራቹን ባለማቋረጥ በመናፈቅ እንደሆነ እየነገረን ነው፡፡ ኢየሱስ ዘወትር ራሱን ስለልጆቹ እየሰጠ ያለ ልክ እንደ ጡት እንደምትመግብ እናት ነው፡፡ እኛም እንደ ልጆች ወደሚያድነንና ወደሚያቀርብልን ደግመን ደጋግመን ስንመላለስ እናድጋለን፡፡
ብዙውን ጊዜ የምናስበው የድሮ ባህሪያችንን የምንተውበት ሁኔታ ለኃጢአታችን እምቢ በማለት ሲሆን እንዲሁም ሊመጣ ባለው ትንሳኤያችን ላይ ተስፋ የምናደርገው ደግሞ ፊታችንን በመቧጨር፣ ብዙ በመስራትና የበለጠ በመጣር ነው። ጴጥሮስ ግን የሚለን እንደ እግዚአብሔር ልጅነታችን ለማደግ ልክ እንደ መጠጣት፣ እንደ መብላት እና እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል የፈፀመልንን የማመን ያህል ቀላል ነው በማለት ነው፡፡
ህዝቡ እንድንሆን የመረጠንን እግዚአብሔርን ታይ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ዓይኖችህን ያብራልህ፡፡ ኢየሱስ እንዳዳነንና ቅዱስ እንዳደረገን ማየት ይሁንልህ፡፡
ስለዚህ እቅድ

ተስፋ ተኮር በሆነው ደብዳቤው ለመጀመሪያዋ ክፍለ ዘመን ቤተ-ክርስቲያን ጴጥሮስ በማመን፣ በመታዘዝ እና ፍርድና መከራ ሲገጥመን ፀንተን እንድንቆም ያበረታናል፡፡ ይህን የሚያሳስበን ምክንያት ደግሞ በክርስቶስ ማን እንደሆንን፣ ቅዱስ የሆነውን ኑሮ እንኖር ዘንድ ኃይል የሆነልንና ወደፊት ዘላለምን ለመውረስ የምንችል ነን በማለት ነው፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Spoken Gospel ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ http://www.spokengospel.com/