አመለካከታችንን በትክክል መቃኘትናሙና

አመለካከታችንን በትክክል መቃኘት

ቀን {{ቀን}} ከ4

የዕይታ ጉልበት

ዕይታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚሰጥ ትልቅ  በረከት ነው። የአንድ አማኝ ሀብት የሚለካው በገንዘብ ሳይሆን በዕይታ ጥራት ነው። የክርስቲያን ጉልበት በማየት ውስጥ ይገለጣል። ሰውን የሚያፀናው ዕይታ ነው። ዕይታ ሰውን ተሸናፊ ወይም አሸናፊ  ያደርጋል። 

ኤልሳና ግያዝን የገጠማቸው ፈተና ተመሳሳይ ነበር። ይሁን እንጂ ዕይታ በሁለቱ ሰዎች መሀከል ልዩነት ፈጠረ። ግያዝ በስጋ አይን ጠላትን ተመልክቶ ወዮልን እያለ መርዶ ሲያወራ ኤልሳዕ ግን በመንፈሱ እግዚአብሔርን አይቶ የድል ዜና አመጣ። አንዱ አይቶ ሲደክም ሌላው አይቶ በረታ። ርግጥ ነው:- በአማኞች ህይወት  ላይ ብዙ ፈተና ተደቅኗል። 

ፈተና የእግዚአብሔርን ክብር ይገልጣል እንጅ ለአማኝ ህይወት ውድቀት አይሆንም። ምክንያቱም ዓለም ላይ ካለው ፈተና በላይ በአማኞች ህይወት ውስጥ ያለው እግዚአብሔር ሀያል ነው። ነገር ግን አንዳንዶች የብጭቆውን ግማሽ ባዶነት አይተው ተስፋ ሲቆርጡ ሌሎች ደግሞ የብርጭቆውን ግማሽ ሙሉነት አይተው ተስፋን ይሰንቃሉ። ስለዚህ ዓለም ላይ ከሚናፈስ ወሬ ተለይተን ከእግዚአብሔር ጋር በመጣበቅ አይን የሚከፍተውን ቃል ዕለት ተለት መመገብ ያስፈልገናል።

የሕይወት ተዛምዶ

አንተ ልብ ውስጥ ያለውን ነገር ወደ ፍፃሜ የሚያመጣው ዕይታ ነው።  ያንተን ሠላምና ረፍት የሚጠበቀው በውስጥ  ዕይታ እንጅ በውጭ ፈተና አይደለም። ስለዚህ ትውልዱን በተገዳደረ ፈተና ላይ  እንደ አይን ብሌን የሚጠብቅህን እግዚአብሔር አይተህ የድል ዜና ታበስራለህ ወይስ እንደ ግያዝ በዙሪያህ ያለውን ፈተና አይተህ ወዮልን ትላለህ?

ፀሎት

እግዚአብሔር  ሆይ፥ ዓለም ላይ ካለው ፈተና ይልቅ ያንተን ሀያልነት እናይ ዘንድ በኢየሱስ ስም የልብ አይናችን ይከፈት። አሜን!


ቅዱሳት መጻሕፍት

ስለዚህ እቅድ

አመለካከታችንን በትክክል መቃኘት

አመለካከትዎን መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ቃል በማስተካከል 4ቱን ቀናት ያሳልፉ። የመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ በድል ለመጓዝ የእግዚአብሔርን አመለካከት እንዴት እንደጠበቁ ከተለያዩ ታሪኮች ይማሩ።

More

ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://bezainternational.org