መዝሙር 68:11-20

መዝሙር 68:11-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ማቅ ለበ​ስሁ መተ​ረ​ቻም ሆን​ሁ​ላ​ቸው። በደጅ የሚ​ቀ​መጡ በእኔ ይጫ​ወ​ታሉ፤ ወይን የሚ​ጠ​ጡም በእኔ ይዘ​ፍ​ናሉ። እኔስ በጸ​ሎቴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታው በጊ​ዜው ነው፤ ይቅ​ር​ታህ ብዙ ሲሆን መድ​ኃ​ኒቴ ሆይ፥ በእ​ው​ነት አድ​ነኝ። እን​ዳ​ይ​ው​ጠኝ ከረ​ግ​ረግ አው​ጣኝ፤ ከጠ​ላ​ቶ​ችና ከጥ​ልቅ ውኃ አስ​ጥ​ለኝ። የውኃ ማዕ​በል አያ​ስ​ጥ​መኝ፥ ጥል​ቁም አይ​ዋ​ጠኝ፥ ጕድ​ጓ​ዶ​ችም አፋ​ቸ​ውን በኔ ላይ አይ​ክ​ፈቱ፤ አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ መል​ካም ናትና ስማኝ፤ እንደ ይቅ​ር​ታ​ህም ብዛት ወደ እኔ ተመ​ል​ከት፤ ከባ​ሪ​ያ​ህም ፊት​ህን አት​መ​ልስ፤ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለ​ሁና ፈጥ​ነህ ስማኝ። ነፍ​ሴን ተመ​ል​ክ​ተህ ተቤ​ዣት፤ ስለ ጠላ​ቶ​ችም አድ​ነኝ። አንተ ስድ​ቤን፥ እፍ​ረ​ቴ​ንም፥ ነው​ሬ​ንም ታው​ቃ​ለህ፤ በሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ሁሉ ፊት። ሰው​ነቴ ስድ​ብ​ንና ውር​ደ​ትን ታገ​ሠች፤ አዝኜ ተቀ​መ​ጥሁ፥ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ኝ​ም አጣሁ።

መዝሙር 68:11-20 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ጌታ እንዲህ ሲል ቃሉን አስተላለፈ፤ ትእዛዙን የሚያውጁትም ብዙ ሰራዊት ናቸው፤ “የሰራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ፤ በሰፈር የዋሉ ሴቶችም ምርኮን ተካፈሉ። በበጎች በረት መካከል ብትገኙ እንኳ፣ ከብር እንደ ተሠሩ የርግብ ክንፎች፣ በቅጠልያ ወርቅ እንደ ተለበጡ ላባዎች ናችሁ።” ሁሉን ቻዩ በዚያ የነበሩትን ነገሥታት በበተነ ጊዜ፣ በሰልሞን እንደሚወርድ በረዶ አደረጋቸው። አንተ ብርቱ ተራራ፣ የባሳን ተራራ ሆይ፤ አንተ ባለብዙ ጫፍ ተራራ፣ የባሳን ተራራ፤ እናንተ ባለብዙ ጫፍ ተራሮች ሆይ፤ እግዚአብሔር ሊኖርበት የመረጠውን ተራራ፣ በርግጥ እግዚአብሔር ለዘላለም የሚኖርበትን ተራራ ለምን በቅናት ዐይን ታያላችሁ? የእግዚአብሔር ሠረገላዎች እልፍ አእላፍ ናቸው፤ ሺሕ ጊዜም ሺሕ ናቸው፤ ጌታ ከሲና ወደ መቅደሱ ገባ። ወደ ላይ ዐረግህ፤ ምርኮ አጋበስህ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ አንተ በዚያ ትኖር ዘንድ፣ ከዐመፀኞችም ሳይቀር፣ ከሰዎች ስጦታን ተቀበልህ። ሸክማችንን በየዕለቱ የሚሸከምልን፣ አዳኝ አምላካችን፣ ጌታ ይባረክ። ሴላ አምላካችን የሚያድን አምላክ ነው፤ ከሞት ማምለጥ የሚቻለውም በጌታ በእግዚአብሔር ነው።

መዝሙር 68:11-20 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጠ፤ ብዙ ሴቶችም ዜናውን አሠራጩ፤ እንዲህም አሉ፦ “ነገሥታት ከነሠራዊታቸው ወደ ኋላቸው ሸሹ! በቤት የቀሩ ሴቶችም ምርኮን ተካፈሉ፤ በጎቹን ለመጠበቅ ወደ ኋላ የቀሩት ክንፎቻቸው በብር የተለበዱ አንጸባራቂ የሆኑ ከወርቅ የተሠሩ ላባ ያላቸው ማዕድናዊ ርግቦችን አገኙ፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ነገሥታትን በበታተነ ጊዜ በረዶ በጻልሞን ተራራዎች ላይ እንዲዘንብ አደረገ። “የባሳን ተራራ ብዙ ወጣ ገባ የሆነና ግርማ ያለው ተራራ ነው። እናንተ ባለ ብዙ ወጣ ገብ ተራራዎች፥ እግዚአብሔር ሊኖርበት ወደ መረጠው ተራራ በቅናት የምትመለከቱት ለምንድን ነው? በዚያ እኮ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይኖርበታል። “እግዚአብሔር በብዙ ሺህ ከሚቈጠሩት ታላላቅ ሠረገላዎች ጋር ከሲና ወደ ተቀደሰው መቅደሱ ይመጣል። እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ወደ ላይ ወደ መኖሪያህ በወጣህ ጊዜ ምርኮን ይዘህ ሄድክ፤ ከዐመፀኞች እንኳ ሳይቀር ከሰዎች ሁሉ ምርኮን ተቀበልክ። “ሸክማችንን በየቀኑ የሚያቀልልንና እኛን የሚያድን እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን። አምላካችን የሚያድን አምላክ ነው፤ ከሞት እንድናመልጥ የሚያደርገን ጌታ እግዚአብሔር ነው።

መዝሙር 68:11-20 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እንስሶችህ በውስጡ አደሩ፥ አቤቱ፥ በቸርነትህ ለድሆች አዘጋጀህ። ጌታ ትእዛዙን ሰጠ፥ የሚያበሥሩት ብዙ ሠራዊት ናቸው። የሠራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ፥ በቤትም የምትኖር ምርኮን ተካፈለች። በርስቶች መካከል ብታድሩ፥ ከብር እንደ ተሠሩ እንደ ርግብ ክንፎች፥ በቅጠልያ ወርቅም እንደ ተለበጡ ላባዎችዋ ትሆናላችሁ። ሰማያዊ ንጉሥ በላይዋ ባዘዘ ጊዜ፥ በሰልሞን ላይ በረዶ ዘነበ። መለኮታዊ ተራራ፥ የባሳን ተራራ፥ የጸና ተራራና የባሳን ተራራ። ጽኑ ተራራዎች ሆይ ለምን በቅናት ታያላችሁ? እግዚአብሔር ይህን ተራራ ያድርበት ዘንድ ወደደው፥ በእውነት ጌታ ለዘለዓለም ያድርበታል። የእግዚአብሔር ሠረገላዎች የብዙ ብዙ ሺህ ናቸው፥ ጌታ በመቅደሱ በሲና በመካከላቸው ነው። ወደ ላይ ዓረግህ፥ ምርኮን ማረክህ፥ ስጦታንም ከሰዎች ወሰድህ፥ ከዓመፀኞችም ጭምር፥ በዚያም ጌታ ያድር ዘንድ። በየዕለቱ የሚንከባከበን ጌታ የተመሰገነ ይሁን፥ እግዚአብሔር ያድነናል።