እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጠ፤ ብዙ ሴቶችም ዜናውን አሠራጩ፤ እንዲህም አሉ፦ “ነገሥታት ከነሠራዊታቸው ወደ ኋላቸው ሸሹ! በቤት የቀሩ ሴቶችም ምርኮን ተካፈሉ፤ በጎቹን ለመጠበቅ ወደ ኋላ የቀሩት ክንፎቻቸው በብር የተለበዱ አንጸባራቂ የሆኑ ከወርቅ የተሠሩ ላባ ያላቸው ማዕድናዊ ርግቦችን አገኙ፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ነገሥታትን በበታተነ ጊዜ በረዶ በጻልሞን ተራራዎች ላይ እንዲዘንብ አደረገ። “የባሳን ተራራ ብዙ ወጣ ገባ የሆነና ግርማ ያለው ተራራ ነው። እናንተ ባለ ብዙ ወጣ ገብ ተራራዎች፥ እግዚአብሔር ሊኖርበት ወደ መረጠው ተራራ በቅናት የምትመለከቱት ለምንድን ነው? በዚያ እኮ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይኖርበታል። “እግዚአብሔር በብዙ ሺህ ከሚቈጠሩት ታላላቅ ሠረገላዎች ጋር ከሲና ወደ ተቀደሰው መቅደሱ ይመጣል። እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ወደ ላይ ወደ መኖሪያህ በወጣህ ጊዜ ምርኮን ይዘህ ሄድክ፤ ከዐመፀኞች እንኳ ሳይቀር ከሰዎች ሁሉ ምርኮን ተቀበልክ። “ሸክማችንን በየቀኑ የሚያቀልልንና እኛን የሚያድን እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን። አምላካችን የሚያድን አምላክ ነው፤ ከሞት እንድናመልጥ የሚያደርገን ጌታ እግዚአብሔር ነው።
መጽሐፈ መዝሙር 68 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 68:11-20
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች