መዝሙር 2:7-11
መዝሙር 2:7-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እናገር ዘንድ፥ እግዚአብሔር አለኝ፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔም ዛሬ ወለድሁህ። ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ፥ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ። በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀጠቅጣቸዋለህ።” አሁንም እናንት ነገሥታት፥ ልብ አድርጉ፤ እናንት የምድር ፈራጆችም፥ ተገሠጹ። ለእግዚአብሔር በፍርሀት ተገዙ፥ በረዓድም ደስ ይበላችሁ።
ያጋሩ
መዝሙር 2 ያንብቡመዝሙር 2:7-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የእግዚአብሔርን ሕግ ዐውጃለሁ፤ እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤ ለምነኝ፤ መንግሥታትን ርስት አድርጌ፣ የምድርንም ዳርቻ ግዛት እንዲሆንህ እሰጥሃለሁ። አንተም በብረት በትር ትቀጠቅጣቸዋለህ፤ እንደ ሸክላ ዕቃ ታደቅቃቸዋለህ።” ስለዚህ እናንተ ነገሥታት ልብ በሉ፤ እናንተ የምድር ገዦችም፣ ተጠንቀቁ። እግዚአብሔርን በፍርሀት አገልግሉት፤ ለርሱ በመንቀጥቀጥ ደስ ያሰኛችሁ።
ያጋሩ
መዝሙር 2 ያንብቡ