መዝ​ሙረ ዳዊት 2:7-11

መዝ​ሙረ ዳዊት 2:7-11 አማ2000

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እና​ገር ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለኝ፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔም ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ። ለም​ነኝ፥ አሕ​ዛ​ብን ለር​ስ​ትህ የም​ድ​ር​ንም ዳርቻ፥ ለግ​ዛ​ትህ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ። በብ​ረት በትር ትጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።” አሁ​ንም እና​ንት ነገ​ሥ​ታት፥ ልብ አድ​ርጉ፤ እና​ንት የም​ድር ፈራ​ጆ​ችም፥ ተገ​ሠጹ። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፍ​ር​ሀት ተገዙ፥ በረ​ዓ​ድም ደስ ይበ​ላ​ችሁ።