መዝሙር 19:7-9 - Compare All Versions

መዝሙር 19:7-9 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስንም መልሶ ያለመልማል፤ የእግዚአብሔር ሥርዐት የታመነ ነው፤ አላዋቂውን ጥበበኛ ያደርጋል። የእግዚአብሔር ሕግጋት ትክክል ናቸው፤ ልብን ደስ ያሰኛሉ። የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ ዐይንን ያበራል። እግዚአብሔርን መፍራት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። የእግዚአብሔር ፍርድ የታመነ፣ ሁለንተናውም ጻድቅ ነው።

መዝሙር 19:7-9 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ለነፍስ አዲስ ሕይወትን ይሰጣል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ የታመነ ነው፤ ማስተዋል ለጐደላቸው ጥበብን ይሰጣል። የእግዚአብሔር ሕግ ትክክል ነው፤ ለልብ ደስታን ይሰጣል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ ለዐይን ብርሃንን ይሰጣል። እግዚአብሔርን መፍራት ለዘለዓለም የሚኖር ንጽሕና ነው፤ የእግዚአብሔር ፍርዶች ሁሉ እያንዳንዳቸው እውነትና ጽድቅ ናቸው።

መዝሙር 19:7-9 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እነ​ዚያ በፈ​ረ​ሶ​ችና በሰ​ረ​ገ​ላ​ዎች ይታ​መ​ናሉ፤ እኛ ግን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ከፍ ከፍ እን​ላ​ለን። እነ​ርሱ ተሰ​ነ​ካ​ክ​ለው ወደቁ፤ እኛ ግን ተነ​ሣን፥ ጸን​ተ​ንም ቆምን። አቤቱ፥ ንጉ​ሥን አድ​ነው፥ በም​ን​ጠ​ራ​ህም ቀን ስማን።

መዝሙር 19:7-9 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

አወጣጡ ከሰማያት ዳርቻ ነው፥ ዙሪቱም እስከ ዳርቻቸው ነው፥ ከትኩሳቱም የሚሰወር የለም። የጌታ ሕግ ፍጹም ነው፥ ነፍስን ይመልሳል፥ የጌታ ምስክር የታመነ ነው፥ የዋሆችን ጠቢባን ያደርጋል። የጌታ ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፥ የጌታ ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል።