መዝሙር 147:15-18
መዝሙር 147:15-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል፤ ቃሉም እጅግ በፍጥነት ይሮጣል። ዐመዳዩን እንደ በርኖስ ይዘረጋል፤ ውርጩን እንደ ዐመድ ይነሰንሳል። የበረዶውን ድንጋይ ቍልቍል ይወረውረዋል፤ በውሽንፍሩስ ቅዝቃዜ ፊት ማን ሊቆም ይችላል? ቃሉን ልኮ ያቀልጣቸዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፤ ውሆችንም ያፈስሳል።