መጽሐፈ መዝሙር 147:15-18

መጽሐፈ መዝሙር 147:15-18 አማ05

ለምድር ትእዛዙን ያስተላልፋል፤ ቃሉም ወዲያው ይፈጸማል። ዐመዳዩን እንደ ባዘቶ ያነጥፈዋል፤ ውርጩንም እንደ ዐመድ ይበትነዋል። በረዶውንም እንደ ጠጠር አድርጎ ያወርደዋል፤ እርሱ የሚልከውን ውርጭ ማንም ሊቋቋመው አይችልም። ከዚህ በኋላ ትእዛዝ ይሰጣል፤ የተጋገረውም በረዶ ይቀልጣል፤ ነፋስን ያነፍሳል፤ ውሃም ይፈስሳል።