ምሳሌ 8:11-14 - Compare All Versions
ምሳሌ 8:11-14 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ጥበብ ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናትና፤ ከምትመኙት ነገር ሁሉ አንዳች የሚስተካከላት የለም። “እኔ ጥበብ ከማስተዋል ጋራ አብሬ እኖራለሁ፤ ዕውቀትና ልባምነት ገንዘቦቼ ናቸው። እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን መጥላት ነው፤ እኔም ትዕቢትንና እብሪትን፣ ክፉ ጠባይንና ጠማማ ንግግርን እጠላለሁ። ምክርና ትክክለኛ ጥበብ የእኔ ናቸው፤ ማስተዋል አለኝ፤ ብርታት አለኝ።
ምሳሌ 8:11-14 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
“እኔ ጥበብ፥ ከዕንቊ የምበልጥ ስለ ሆንኩ ምንም ነገር ብትመኙ ከእኔ የሚወዳደር አንድም ነገር የለም። እኔ ጥበብ፥ ማስተዋል አለኝ፤ ዕውቀትና ትክክለኛ አስተያየት የእኔ ናቸው። ክፉ ነገርን መጥላት እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ እኔ ትዕቢትንና ዕብሪትን እጠላለሁ፤ ክፉ መንገድንና ጠማማ ንግግርን አልወድም ምክርና መልካም ጥበብ ከእኔ ይገኛሉ፤ ማስተዋልና ብርታትም የእኔ ናቸው።
ምሳሌ 8:11-14 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ዋጋው ብዙ ከሆነ ዕንቍ ጥበብ ትበልጣለችና፥ የከበረ ነገር ሁሉ አይተካከላትም። እኔ ጥበብ ምክርን አሳደርሁ፥ ዕውቀትንና ዐሳብንም እኔ ጠራሁ። እግዚአብሔርን የሚፈራ ዐመፃን ይጠላል፤ ጥልንና ትዕቢትን፥ ክፉ መንገድንም ይጠላል። የክፉ ሰዎችንም ጠማማ መንገድ ጠላሁ። ምክርና ሥልጣን የእኔ ናቸው፤ ማስተዋል የእኔ ነው፥ ብርታትም የእኔ ነው።
ምሳሌ 8:11-14 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ጥበብ ከዕንቁ ትበልጣለችና የከበረ ነገር ሁሉ አይተካከላትም። እኔ ጥበብ፥ በብልሃት ተቀምጫለሁ፥ እውቀትንም ጥንቃቄንም አግኝቻለሁ። ጌታን መፍራት ክፋትን መጥላት ነው፥ ትዕቢትንና እብሪትን ክፉንም መንገድ ጠማማውንም ንግግር እጠላለሁ። ምክርና መልካም ጥበብ የእኔ ነው፥ ማስተዋል እኔ ነኝ፥ ብርታትም አለኝ።