ምሳሌ 8:11-14
ምሳሌ 8:11-14 NASV
ጥበብ ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናትና፤ ከምትመኙት ነገር ሁሉ አንዳች የሚስተካከላት የለም። “እኔ ጥበብ ከማስተዋል ጋራ አብሬ እኖራለሁ፤ ዕውቀትና ልባምነት ገንዘቦቼ ናቸው። እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን መጥላት ነው፤ እኔም ትዕቢትንና እብሪትን፣ ክፉ ጠባይንና ጠማማ ንግግርን እጠላለሁ። ምክርና ትክክለኛ ጥበብ የእኔ ናቸው፤ ማስተዋል አለኝ፤ ብርታት አለኝ።

