ምሳሌ 15:1-4 - Compare All Versions
ምሳሌ 15:1-4 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ቍጣ ጥበበኞችን ታጠፋለች፤ የለዘበ ቃል ቍጣን ይመልሳል፥ ሻካራ ቃል ግን ጠብን ያነሣሣል። የጠቢባን ምላስ መልካም ነገርን ታውቃለች፤ የአላዋቂዎች አፍ ግን ክፋትን ይናገራል። የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉ ቦታ ናቸው፤ ክፉዎችንና ደጎችንም ይመለከታሉ። ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፤ የሚጠብቀው ግን የዕውቀት መንፈስን ይሞላል።
ምሳሌ 15:1-4 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
የለዘበ መልስ ቍጣን ያበርዳል፤ ክፉ ቃል ግን ቍጣን ይጭራል። የጠቢብ አንደበት ዕውቀትን ታወድሳለች፤ የሞኞች አንደበት ግን ቂልነትን ያፈልቃል። የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉም ስፍራ ናቸው፤ ክፉዎችንም ደጎችንም ነቅተው ይመለከታሉ። ፈውስ የምታመጣ ምላስ የሕይወት ዛፍ ናት፤ አታላይ ምላስ ግን መንፈስን ትሰብራለች።
ምሳሌ 15:1-4 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ልዝብ አነጋገር ቊጣን ያስታግሣል፤ የቊጣ አነጋገር ግን ቊጣን ያባብሳል። የጠቢባን አንደበት ዕውቀትን ያፈልቃል። የሞኞች አፍ ግን ሞኝነትን ይለፈልፋል። እግዚአብሔር በየቦታው የሚደረገውን ነገር ሁሉ ያያል። መልካምም ሆነ ክፉ ድርጊትን ይመለከታል። ለስላሳ አነጋገር ሕይወትን ይሰጣል። ተንኰል የተሞላበት አነጋገር ግን መንፈስን ይሰብራል።
ምሳሌ 15:1-4 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
የለዘበች መልስ ቁጣን ትመልሳለች፥ ሸካራ ቃል ግን ቁጣን ታስነሣለች። የጠቢባን ምላስ እውቀትን ያሳምራል፥ የሰነፎች አፍ ግን ስንፍናን ያፈልቃል። የጌታ ዐይኖች በስፍራ ሁሉ ናቸው፥ ክፉዎችንና ደጎችን ይመለከታሉ። ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፥ የጠማማ ምላስ ግን ነፍስን ይሰብራል።