ምሳሌ 1:7-9
ምሳሌ 1:7-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ዕውቀት ለሚያደርጋት ሁሉ መልካም ናት። እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፥ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናትህንም ትእዛዝ ቸል አትበል፤ ለራስህ የክብር ዘውድን ለአንገትህም የወርቅ ድሪ ታገኛለህና።
ያጋሩ
ምሳሌ 1 ያንብቡምሳሌ 1:7-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፤ ቂሎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። ልጄ ሆይ፤ የአባትህን ምክር አድምጥ፤ የእናትህንም ትምህርት አትተው። ለራስህ ሞገስን የሚያጐናጽፍ አክሊል፣ ዐንገትህን የሚያስውብ ድሪ ይሆንልሃል።
ያጋሩ
ምሳሌ 1 ያንብቡምሳሌ 1:7-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ ሞኞች ግን ጥበብና ሥነ ሥርዓትን ይንቃሉ። ልጄ ሆይ! የአባትህን ምክር ስማ፤ እናትህ የምታስተምርህንም ሁሉ አትናቅ። እነርሱም ለራስህ ክብርን እንደሚያቀዳጅ ዘውድ፥ ለአንገትህም ውበትን እንደሚሰጥ ሐብል ይሆኑልሃል።
ያጋሩ
ምሳሌ 1 ያንብቡ