ፊልጵስዩስ 2:20-21 - Compare All Versions
ፊልጵስዩስ 2:20-21 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ከእርሱ በቀር፥ እንደ እኔ ሆኖ በማስተዋል ግዳጃችሁን የሚፈጽም የለኝምና። የክርስቶስን ያይደለ፥ ሁሉም የራሱን ጉዳይ ያስባልና።
ፊልጵስዩስ 2:20-21 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ስለ እናንተ ደኅንነት ከልቡ የሚገድደው እንደ እርሱ ያለ ማንም የለኝም፤ ሁሉም የኢየሱስ ክርስቶስን ሳይሆን የራሳቸውን ፍላጎት ለማሟላት ይሯሯጣሉና።
ፊልጵስዩስ 2:20-21 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
እንደ እርሱ ያለ፥ ስለ ኑሮአችሁ በቅንነት የሚጨነቅ፥ ማንም የለኝምና፤ ሁሉ የራሳቸውን ይፈልጋሉና፥ የክርስቶስ ኢየሱስን አይደለም።
ፊልጵስዩስ 2:20-21 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ስለ እናንተ ሁኔታ ከልብ የሚያስብ ከጢሞቴዎስ በቀር ሌላ ሰው የለኝም። ሌሎቹ ግን የራሳቸውን ጥቅም ብቻ ያሳድዳሉ እንጂ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ግድ የላቸውም።
ፊልጵስዩስ 2:20-21 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
እንደ እኔ ሆኖ ስለ ደኅንነታችሁ በቅንነት የሚጨነቅ እንደ እርሱ ያለ ማንም የለኝምና፤ የተቀሩት ሁሉ ግን የክርስቶስ ኢየሱስን ሳይሆን የራሳቸውን ጥቅም የሚሹ ናቸውና።