ሉቃስ 10:1-4
ሉቃስ 10:1-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከዚህም በኋላ ጌታችን ሌሎች ሰባ ሰዎችን መረጠ፤ ሁለት ሁለት አድርጎም ሊሄድበት ወደ አለው ከተማና መንደር በፊቱ ላካቸው። ጌታችን ኢየሱስም አላቸው፥ “መከሩ ብዙ ነው፤ ሠራተኛው ግን ጥቂት ነው፤ እንግዲህ ለመከሩ ሠራተኛ ጨምሮ ይልክ ዘንድ ባለ መከሩን ለምኑት። ሂዱ፤ እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ። ከረጢትም፥ ስልቻም፥ ጫማም፥ ምንም ምን አትያዙ፤ በመንገድም ማንንም ሰላም አትበሉ።
ሉቃስ 10:1-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚህ በኋላ ጌታ ሌሎች ሰባ ሁለት ሰዎችን መርጦ ሾመ፤ ወደሚሄድበትም ከተማና ቦታ ሁሉ እንዲቀድሙት፣ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ “መከሩ ብዙ ነው፤ ሠራተኞቹ ግን ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህ የመከሩ ጌታ ሠራተኞችን ወደ መከሩ እንዲልክ ለምኑት። ሂዱ፤ እንግዲህ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ። ኰረጆ ወይም ከረጢት ወይም ጫማ አትያዙ፤ በመንገድ ላይም ለማንም ሰላምታ አትስጡ።
ሉቃስ 10:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከዚህም በኋላ ጌታ ሌሎቹን ሰብዓ ሾመ፥ ሁለት ሁለትም አድርጎ እርሱ ሊሄድበት ወዳለው ከተማና ስፍራ ሁሉ በፊቱ ላካቸው። አላቸውም፦ መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ለመከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት። ሂዱ፤ እነሆ፥ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ። ኮረጆም ከረጢትም ጫማም አትያዙ፤ በመንገድም ለማንም እጅ አትንሡ።
ሉቃስ 10:1-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከዚህ በኋላ ጌታ፥ ሌሎች ሰባ ሁለት ሰዎችን መረጠ፤ እርሱ ሊሄድበት ወደአሰበውም ከተማና ቦታ ሁሉ ቀድመውት እንዲሄዱ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው። እንዲህም አላቸው፦ “እነሆ፥ መከሩ ብዙ ነው፤ የመከሩ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህ የመከሩ ጌታ ለመከሩ ሥራ ተጨማሪ ሠራተኞችን እንዲልክ ለምኑት። እንግዲህ ሂዱ፤ እነሆ፥ እንደ በጎች በተኲላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ለመንገዳችሁ ምንም አትያዙ፤ የገንዘብ ቦርሳም ቢሆን፥ ከረጢትም ቢሆን፥ ጫማም ቢሆን አትያዙ፤ ከሰው ጋር ሰላምታ በመለዋወጥ በመንገድ ላይ ቆማችሁ ጊዜ አታጥፉ።
ሉቃስ 10:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከዚህም በኋላ ጌታ ሌሎች ሰባ ሁለት ሰዎችን መረጠ፤ ሁለት ሁለትም አድርጎ ራሱ ሊሄድበት ወደአሰበው ከተማና ስፍራ ሁሉ አስቀድሞ ላካቸው። እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “መከሩ ብዙ ነው፤ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህ የመከሩን ጌታ ለመከሩ ሠራተኞችን እንዲልክ ለምኑት። እንግዲህ ሂዱ፤ እነሆ፥ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ። ቦርሳም ከረጢትም ጫማም አትያዙ፤ በመንገድ ላይ ለማንም ሰላምታን አትስጡ።