የሉ​ቃስ ወን​ጌል 10:1-4

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 10:1-4 አማ2000

ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ሌሎች ሰባ ሰዎ​ችን መረጠ፤ ሁለት ሁለት አድ​ር​ጎም ሊሄ​ድ​በት ወደ አለው ከተ​ማና መን​ደር በፊቱ ላካ​ቸው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም አላ​ቸው፥ “መከሩ ብዙ ነው፤ ሠራ​ተ​ኛው ግን ጥቂት ነው፤ እን​ግ​ዲህ ለመ​ከሩ ሠራ​ተኛ ጨምሮ ይልክ ዘንድ ባለ መከ​ሩን ለም​ኑት። ሂዱ፤ እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተ​ኵ​ላ​ዎች መካ​ከል እል​ካ​ች​ኋ​ለሁ። ከረ​ጢ​ትም፥ ስል​ቻም፥ ጫማም፥ ምንም ምን አት​ያዙ፤ በመ​ን​ገ​ድም ማን​ንም ሰላም አት​በሉ።