ኢያሱ 6:1-7

ኢያሱ 6:1-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ኢያ​ሪ​ኮም በግ​ንብ ታጥራ ተዘ​ግታ ነበር፤ ወደ እር​ስዋ የሚ​ገባ፥ ከእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ወጣ አል​ነ​በ​ረም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን አለው፥ “እነሆ፥ ኢያ​ሪ​ኮ​ንና ንጉ​ሥ​ዋን ጽኑ​ዓን፥ ኀያ​ላ​ን​ዋ​ንም በእ​ጅህ ሰጥ​ቼ​አ​ለሁ። አን​ተም ተዋ​ጊ​ዎ​ችን ሁሉ በዙ​ሪ​ያው አሰ​ል​ፋ​ቸው። ተዋ​ጊ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ አንድ ጊዜ ይዙሩ፤ እን​ዲ​ሁም ስድ​ስት ቀን አድ​ርጉ። ሰባ​ትም ካህ​ናት ሰባት ቀንደ መለ​ከት በታ​ቦቱ ፊት ይያዙ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፤ ካህ​ና​ቱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ይንፉ። ቀንደ መለ​ከ​ቱም ባለ​ማ​ቋ​ረጥ ሲነፋ፥ የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ ስት​ሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ቅጥር ይወ​ድ​ቃል፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ፊት ለፊት እየ​ሮጠ ይገ​ባ​ባ​ታል።” የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ ካህ​ና​ቱን ጠርቶ፥ “የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ከሙ፤ ሰባ​ትም ካህ​ናት ሰባት ቀንደ መለ​ከት ወስ​ደው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሂዱ” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡ​ንም፥ “ሂዱ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ዙሩ፤ ተዋ​ጊ​ዎ​ችም ከጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሂዱ ብላ​ችሁ እዘ​ዙ​አ​ቸው” አላ​ቸው።

ኢያሱ 6:1-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚህ ጊዜ እስራኤላውያንን ከመፍራት የተነሣ፣ ኢያሪኮ ፈጽማ ተዘግታ ነበር፤ ወደ ውጭ የሚወጣም ሆነ ወደ ውስጥ የሚገባ አልነበረም። እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፤ ኢያሪኮን ከንጉሥዋና ከተዋጊዎቿ ጋራ አሳልፌ በእጅህ ሰጥቻለሁ። ከተማዪቱን ከተዋጊዎቻችሁ ጋራ አንድ ጊዜ ዙሩ፤ ይህንም ስድስት ቀን አድርጉ። ሰባት ካህናት፣ ሰባት ቀንደ መለከት ተሸክመው በታቦቱ ፊት ይውጡ፤ በሰባተኛውም ቀን ካህናቱ መለከት እየነፉ ከተማዪቱን ሰባት ጊዜ ይዙሩ። የማያቋርጥ የመለከት ድምፅ ሲነፋ በምትሰሙበት ጊዜ፣ ሕዝቡ ሁሉ ከፍ ያለ ጩኸት ያሰማ፤ ከዚያም የከተማዪቱ ቅጥር ይፈርሳል፤ ሕዝቡም ወደ ላይ ይወጣል፤ እያንዳንዱም ሰው በቀጥታ ይገባል።” ስለዚህ የነዌ ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ፣ “የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፤ ሰባት ካህናትም ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ” አላቸው። ሕዝቡንም፣ “ወደ ፊት ሂዱ፤ ከተማዋን ዙሩ፤ የታጠቁ ተዋጊዎችም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ቀድመው ይሂዱ፤ ከተማዪቱንም ዙሩ” ሲል አዘዛቸው።

ኢያሱ 6:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ኢያሪኮም ከእስራኤል ልጆች የተነሣ ፈጽማ ተዘግታ ነበር፥ ወደ እርስዋ የሚገባ ከእርስዋም የሚወጣ ማንም አልነበረም። እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፦ ተመልከት፥ ኢያሪኮንና ንጉሥዋን ጽኑዓን ኃያላንዋንም በእጅህ ሰጥቼአለሁ። ሰልፈኞቻችሁ ሁሉ ከተማይቱን አንድ ጊዜ ይዙሩአት፥ እንዲሁም ስድስት ቀን አድርጉ። ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይሸከሙ፥ በሰባተኛውም ቀን ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ። ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ፥ የመለከቱን ድምፅ ስትሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፥ የከተማይቱም ቅጥር ይወድቃል፥ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ አቅንቶ ይገባባታል። የነዌም ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ፦ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፥ ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ወስደው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አላቸው። ሕዝቡንም፦ ሂዱ፥ ከተማይቱንም ዙሩ፥ ሰልፈኞችም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አለ።

ኢያሱ 6:1-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እስራኤላውያንን ከመፍራት የተነሣ የኢያሪኮ ቅጽር በሮች ተዘግተው ነበር፤ ወደ ከተማይቱ መግባትም ሆነ መውጣት የሚችል ማንም አልነበረም፤ እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “ኢያሪኮን ከንጉሥዋና ከወታደሮችዋ ጋር በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ አንተና ወታደሮችህ እስከ ስድስት ቀን ድረስ በቀን አንድ ጊዜ የከተማይቱን ቅጽር በሰልፍ ትዞሩአታላችሁ። እያንዳንዳቸው እምቢልታ የያዙ ሰባት ካህናት ከቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ቀድመው ይሂዱ፤ በሰባተኛው ቀን ካህናቱ እምቢልታ እየነፉ አንተና ወታደሮችህ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ትዞሩአታላችሁ፤ ከዚያን በኋላ ካህናቱ በእምቢልታቸው ከፍተኛ ድምፅ እንዲሰማ ያድርጉ፤ እርሱንም እንደ ሰማችሁ ወዲያውኑ ሰዎቹ ሁሉ በከፍተኛ ድምፅ ይጩኹ፤ የከተማይቱም ቅጽር ይፈርሳል፤ ከዚህም በኋላ መላው ሠራዊት ወደ ከተማይቱ ሰተት ብሎ በቀጥታ ይግባ።” ኢያሱም ካህናቱን ጠርቶ “የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፤ ከእናንተም ሰባታችሁ እምቢልታ ይዛችሁ ከታቦቱ ፊት ቅደሙ።” ሕዝቡንም እንዲህ ሲል አዘዘ፦ “ሂዱ፤ ከተማይቱን ዙሩ፤ ወታደሮቹም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ”።

ኢያሱ 6:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ኢያሪኮም ከእስራኤል ልጆች የተነሣ ፈጽማ ተዘግታ ነበር፤ ወደ እርሷ የሚገባ ከእርሷም የሚወጣ ማንም አልነበረም። ጌታም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ተመልከት፥ ኢያሪኮንና ንጉሥዋን ጽኑዓን ኃያላንዋንም በእጅህ ሰጥቼአለሁ። እናንተም ከተማይቱን ትዞሩአታላችሁ፥ ተዋጊዎቻችሁም ሁሉ ከተማይቱን በቀን አንድ ጊዜ ይዙሩአት፤ እንዲሁም ስድስት ቀን አድርጉ። ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይሸከሙ፤ በሰባተኛውም ቀን ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ። ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ፥ የመለከቱን ድምፅ ስትሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፤ የከተማይቱም ቅጥር ይወድቃል፥ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ ወደ እርሷ አቅንቶ በቀጥታ ይገባል።” የነዌም ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “የቃል ኪዳኑን ታቦት አንሱ፥ ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በጌታ ታቦት ፊት ይሸከሙ።” ሕዝቡንም እንዲህ አለ፦ “ሂዱ፥ ከተማይቱንም ዙሩ፥ ተዋጊዎቹም በጌታ ታቦት ፊት ይሂዱ።”