ኢያሱ 21:20-45

ኢያሱ 21:20-45 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ለቀ​ሩ​ትም ለሌ​ዋ​ው​ያኑ ለቀ​ዓት ልጆች የዕ​ጣ​ቸው ከተ​ሞች ከኤ​ፍ​ሬም ነገድ ደረ​ሱ​አ​ቸው። ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን ሴኬ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጌዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ቄብ​ጻ​ይ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቤቶ​ሮ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። ከዳ​ንም ነገድ ኤል​ቆ​ታ​ይ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ገባ​ቶ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ኤሎ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጌቴ​ራ​ሞ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ጠና​ሕ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዬባ​ታ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሁለ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። የቀ​ሩት የቀ​ዓት ልጆች ወገ​ኖች ከተ​ሞች ሁሉ ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ጋር ዐሥር ናቸው። ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ወገ​ኖች ለጌ​ድ​ሶን ልጆች ከም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ በባ​ሳን ውስጥ የሆ​ነ​ች​ውን ጎላ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቦሶ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሁለ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። ከይ​ሳ​ኮ​ርም ነገድ ቂሶ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዳብ​ራ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሬማ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዓይ​ን​ጋ​ኒ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። ከአ​ሴ​ርም ነገድ መሴ​ላ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ አቤ​ዶ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ሔል​ቃ​ት​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ረዓ​ብ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱ​ንም ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን በገ​ሊላ ውስጥ ቃዴ​ስ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኤማ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃር​ቴ​ን​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፤ ሦስ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። የጌ​ድ​ሶን ልጆች ከተ​ሞች ሁሉ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞች ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ጋር ናቸው። ከሌ​ዋ​ው​ያን ለቀ​ሩት ለሜ​ራሪ ልጆች ወገን ከዛ​ብ​ሎን ነገድ ዮቅ​ና​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃዴ​ስ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዲም​ና​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ሴላ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ። በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል ከሮ​ቤል ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ በሚ​ሶን ምድረ በዳ ቦሶ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኢያ​ዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ቄዴ​ሞ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ሜፍ​ዐ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ። ከጋ​ድም ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን በገ​ለ​ዓድ ውስጥ ራሞ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃሚ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሐሴ​ቦ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኢያ​ዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ። ከሌዊ ወገ​ኖች የቀ​ሩት የሜ​ራሪ ልጆች ከተ​ሞች ሁሉ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ነበሩ፤ ዕጣ​ቸ​ውም ዐሥራ ሁለት ከተማ ነበረ። በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት መካ​ከል የነ​በ​ሩት የሌ​ዋ​ው​ያን ከተ​ሞች ሁሉ በእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች ዙሪያ ካሉ ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር አርባ ስም​ንት ከተ​ሞች ነበሩ። እነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ጋር ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች ሁሉ እን​ዲሁ ነበሩ። [ኢያ​ሱም በየ​ድ​ን​በ​ሮ​ቻ​ቸው ምድ​ርን ማካ​ፈ​ልን ጨረሰ። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ለኢ​ያሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ድር​ሻ​ውን ሰጡት፤ እርሱ የሚ​ፈ​ል​ጋ​ትን ከተማ በኤ​ፍ​ሬም ተራራ የም​ት​ገ​ኘ​ውን ቴም​ና​ሴ​ራን ሰጡት፤ ከተ​ማም ሠራ​ባት፤ በው​ስ​ጧም ተቀ​መጠ። ኢያ​ሱም በም​ደረ በዳ በመ​ን​ገድ የተ​ወ​ለ​ዱ​ትን የገ​ረ​ዘ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ባል​ጩ​ቶች ወስዶ በቴ​ም​ና​ሴራ አኖ​ራ​ቸው።] እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰጠ፤ ወረ​ሱ​አ​ትም፥ ተቀ​መ​ጡ​ባ​ትም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እንደ ማለ​ላ​ቸው በዙ​ሪ​ያ​ቸው ካሉት አሳ​ረ​ፋ​ቸው፤ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ይቋ​ቋ​ማ​ቸው ዘንድ ማንም ሰው አል​ቻ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከተ​ና​ገ​ረው መል​ካም ነገር ሁሉ ተፈ​ጸመ እንጂ ምንም አል​ቀ​ረም።

ኢያሱ 21:20-45 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የሌዊ ልጅ የቀዓት ጐሣዎች ለሆኑት ለሌሎቹ ደግሞ ከኤፍሬም ነገድ ላይ ተከፍለው የሚከተሉት ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው። በተራራማው በኤፍሬም አገርም ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ሴኬምና ጌዝር፣ ቂብጻይሞና ቤትሖሮን ከነመሰማሪያዎቻቸው አራት ከተሞች ተሰጧቸው። እንዲሁም ከዳን ነገድ፣ ኤልተቄን፣ ገባቶን፤ ኤሎንና ጋትሪሞን ከነመሰማሪያዎቻቸው አራት ከተሞች ተሰጧቸው። ከምናሴ ነገድ፣ እኩሌታ ደግሞ ታዕናክና ጋትሪሞን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሁለት ከተሞች ተሰጧቸው። እነዚህ ዐሥር ከተሞች ሁሉ ከነመሰማሪያዎቻቸው ለተቀሩት የቀዓት ጐሣዎች ተሰጧቸው። የጌርሶን ወገኖች ለሆኑት ለሌሎቹ የሌዊ ጐሣዎች የተሰጧቸው የሚከተሉት ናቸው፤ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ በባሳን ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ከተማ ጎላንና በኤሽትራ እነዚህ ሁለት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤ ከይሳኮር ነገድ፣ ቂሶን፣ ዳብራት፣ የርሙትና ዓይንገኒም፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤ ከአሴር ነገድ፣ ሚሽአል፣ ዓብዶን፣ ሔልቃትና ረአብ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤ ከንፍታሌም ነገድ፣ በገሊላ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ከተማ ቃዴስ፣ ሐሞትዶርና ቀርታን እነዚህ ሦስት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤ ለጌርሶናውያን ጐሣዎች የተመደቡት ከተሞች ሁሉ ከነመሰማሪያዎቻቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ። የሜራሪ ጐሣዎች ለሆኑት ለተቀሩት ሌዋውያን የተሰጧቸው የሚከተሉት ናቸው፤ ከዛብሎን ነገድ፣ ዮቅንዓም፣ ቀርታ፣ ዲሞናና ነህላል፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤ ከሮቤል ነገድ፣ ቦሶር፣ ያሀጽ፣ ቅዴሞትና ሜፍዓት፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤ ከጋድ ነገድ፣ በገለዓድ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ከተማ ራሞት መሃናይም፣ ሐሴቦንና ኢያዜር፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው። የሜራሪ ጐሣዎች ለሆኑት ለተቀሩት ሌዋውያን የተመደቡት ከተሞች ሁሉ ዐሥራ ሁለት ነበሩ። እንግዲህ እስራኤላውያን ርስት አድርገው ከያዙት ምድር ለሌዋውያኑ የተሰጧቸው ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው በአጠቃላይ አርባ ስምንት ነበሩ። እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው በዙሪያቸው መሰማሪያዎች ነበሯቸው፤ መሰማሪያ የሌለው ከተማ አልነበረም። ስለዚህ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ይሰጣቸው ዘንድ የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ እነርሱም ምድሪቱን ወረሱ፣ መኖሪያቸውም አደረጓት። እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፤ አንድም ጠላት ሊቋቋማቸው አልቻለም፤ እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን ሁሉ አሳልፎ በእጃቸው ሰጥቷቸዋልና። እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከሰጠው መልካም የተስፋ ቃል አንዳችም አልቀረም፤ ሁሉም ተፈጽሟል።

ኢያሱ 21:20-45 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ወገኖች ሌዋውያን የዕጣቸው ከተሞች ከኤፍሬም ነገድ ደረሱአቸው። በኤፍሬም ተራራማ አገር ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ሴኬምንና መሰምርያዋን፥ ጌዝርንና መሰምርያዋን፥ ቂብጻይምንና መሰምርያዋን፥ ቤትሖሮንንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። ከዳንም ነገድ ኤልተቄንና መሰምርያዋን፥ ገባቶንንና መሰምርያዋን፥ ኤሎንንና መሰምርያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ታዕናክንና መሰምርያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰምርያዋን፥ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው። የቀሩት የቀዓት ልጆች ወገኖች ከተሞች ሁሉ ከመሰምርያቸው ጋር አሥር ናቸው። ለሌዋውያንም ወገኖች ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ በባሳን ውስጥ የሆነቸውን ጎላንንና መሰምርያዋን፥ በኤሽትራንና መሰምርያዋን፥ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው። ከይሳኮርም ነገድ ቂሶንንና መሰምርያዋን፥ ዳብራትንና መሰምርያዋን፥ የርሙትንና መሰምርያዋን፥ ዓይንጋኒምንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። ከአሴርም ነገድ ሚሽአልንና መሰምርያዋን፥ ዓብዶንንና መሰምርያዋን፥ ሔልቃትንና መሰምርያዋን፥ ረአብንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። ከንፍታሌምም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነቸውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰምርያዋን፥ ሐሞትዶንና መሰምርያዋን፥ ቀርታንንና መሰምርያዋን፥ ሦስቱን ከተሞች ሰጡአቸው። የጌድሶን ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው አሥራ ሦስት ከተሞች ከመሰምርያቸው ጋር ናቸው። ከሌዋውያንም ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ወገን ከዛብሎን ነገድ ዮቅንዓምንና መሰምርያዋን፥ ቀርታንና መሰምርያዋን፥ ዲሞናንና መሰምርያዋን፥ ነህላልንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡ። ከሮቤልም ነገድ ቦሶርንና መሰምርያዋን፥ ያሀጽንና መሰምርያዋን፥ ቅዴሞትንና መሰምርያዋን፥ ሜፍዓትንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡ። ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰምርያዋን፥ መሃናይምንና መሰምርያዋን፥ ሐሴቦንንና መሰምርያዋን፥ ኢያዜርንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡ። ከሌዋውያን ወገኖች የቀሩት የሜራሪ ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፥ ዕጣቸውም አሥራ ሁለት ከተማ ነበረ። በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ አርባ ስምንት ከተሞችና መሰምርያቸው ነበሩ። እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው ከመሰምርያቸው ጋር ነበሩ፥ እነዚህም ከተሞች ሁሉ እንዲሁ ነበሩ። እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸው ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። እግዚአብሔርም ለአባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፥ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ ይቋቋማቸው ዘንድ ማንም ሰው አልቻለም፥ እግዚአብሔርም ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።

ኢያሱ 21:20-45 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ለቀሩት ከሌዊ ነገድ ለሆኑት የቀዓት ጐሣዎች ከኤፍሬም ነገድ ይዞታ ተከፍሎ ተሰጣቸው። ለእነርሱም የተሰጡት አራት ከተሞች ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው ሴኬምና በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የሚገኙት የግጦሽ መሬቶችዋ፥ ጌዜር፥ ቂብጻይምና ቤትሖሮን የተባሉት ከግጦሽ መሬቶቻቸው ጋር ናቸው። ከዳን ግዛት ተከፍለው የተሰጡአቸውም አራት ከተሞች ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ኤልተቄ፥ ጊበቶን፥ አያሎንና ጋትሪሞን ናቸው። ከምዕራብ ምናሴ ግዛት ተከፍለው የተሰጡአቸውም ሁለት ከተሞች ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ታዕናክና ጋትሪሞን ናቸው፤ እነዚህ የቀሩት የቀዓት ጐሣ ከግጦሽ ምድራቸው ጋር በድምሩ ዐሥር ከተሞች ተረከቡ። የጌርሾን ጐሣ የሆነው ሌላው የሌዋውያን ወገን ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ከምሥራቅ ምናሴ ግዛት ተከፍለው የተሰጡት ሁለት ከተሞች በባሳን ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው ጎላን ከግጦሽ ምድራቸው ጋር በዔሽተራ ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ናቸው፤ ከይሳኮር ግዛትም ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው አራት ከተሞች፥ ቂሽዮን፥ ዳብራት፥ ያርሙትና ዔንጋኒም ናቸው፤ ከአሴር ግዛትም ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው አራት ከተሞች፥ ሚሽአል፥ ዓብዶን፥ ሔልቃትና ረሖብ ናቸው፤ ከንፍታሌም ግዛት ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው ሦስት ከተሞች በገሊላ ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው ቄዴሽ፥ ሐሞት፥ ዶርና ቃርታን ናቸው። የጌርሾን ጐሣ በሙሉ በድምሩ ዐሥራ ሦስት ከተሞችን ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ተረከቡ። ከመራሪ የተወለዱትም ቀሪዎቹ ሌዋውያን ከዛብሎን ግዛት ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተረከቡአቸው አራት ከተሞች ዮቅነዓም፥ ቃርታ፥ ዲምናና ናህላል ናቸው። ከሮቤል ግዛትም ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው አራት ከተሞች ቤጼር፥ ያሀጽ፥ ቀዴሞትና ሜፋዓት ናቸው፤ ከጋድ ግዛት ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው አራት ከተሞች ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው በገለዓድ ግዛት የምትገኘው ራሞት፥ ማሕናይም፥ ሐሴቦንና ያዕዜር ናቸው፤ የሌዋውያን ነገድ ለሆኑት ለቀሪዎቹ የሜራሪ ጐሣዎች የተሰጡት ዐሥራ ሁለት ከተሞች ናቸው። በእስራኤላውያን ይዞታ ሥር የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ከግጦሽ መሬታቸው ጋር አርባ ስምንት ነበሩ። በእነዚህም መሬቶች በእያንዳንዱ ዘሪያ የግጦሽ መሬት ነበራቸው። ስለዚህ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ሊሰጣቸው በመሐላ ቃል የገባላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤላውያን ሰጠ። ምድሪቱንም ከወረሱ በኋላ በዚያ ተደላድለው ኖሩ፤ እግዚአብሔርም ለቀድሞ አባቶቻቸው በገባው ቃል መሠረት በአካባቢያቸው ሁሉ ሰላምን ሰጣቸው፤ በጠላቶቻቸው ላይ ብዙ ድልን አቀዳጅቶአቸው ስለ ነበረ ከጠላቶቻቸው አንድ እንኳ በፊታቸው ሊቆም አልቻለም። በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት የገባው ቃል ኪዳን ሁሉ ተፈጸመ እንጂ አንድም የቀረ የለም።

ኢያሱ 21:20-45 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች የሌዋውያን ለሆኑ የቀዓት ወገኖች የዕጣቸው ከተሞች ከኤፍሬም ነገድ ደረሱአቸው። እነዚህንም ከተሞች ሰጡአቸው፤ በኤፍሬም ተራራማ አገር ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ሴኬምንና መሰማሪያዋን፥ ጌዝርንና መሰማሪያዋን፥ ቂብጻይምንና መሰማሪያዋን፥ ቤት-ሖሮንንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። ከዳንም ነገድ ኤልተቄንና መሰማሪያዋን፥ ገባቶንንና መሰማሪያዋን፥ ኤሎንንና መሰማሪያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ታዕናክንና መሰማሪያዋን፥ ጋት-ሪሞንንና መሰማሪያዋን፤ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው። የቀሩት የቀዓት ልጆች ወገኖች ከተሞች ሁሉ ከመሰማሪያቸው ጋር ዐሥር ናቸው። ለሌዋውያንም ወገኖች ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ በባሳን ውስጥ የሆነቸውን ጎላንንና መሰማሪያዋን፥ በኤሽትራንና መሰማሪያዋን፤ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው። ከይሳኮርም ነገድ ቂሶንንና መሰማሪያዋን፥ ዳብራትንና መሰማሪያዋን፥ የርሙትንና መሰማሪያዋን፥ ዐይን-ጋኒምንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። ከአሴርም ነገድ ሚሽአልንና መሰማሪያዋን፥ ዓብዶንንና መሰማሪያዋን፥ ሔልቃትንና መሰማሪያዋን፥ ረዓብንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። ከንፍታሌምም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰማሪያዋን፥ ሐሞት-ዶንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንንና መሰማሪያዋን፤ ሦስቱን ከተሞች ሰጡአቸው። የጌድሶን ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው ዐሥራ ሦስት ከተሞች ከመሰማሪያቸው ጋር ነበሩ። ከሌዋውያንም ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ወገን ከዛብሎን ነገድ ዮቅንዓምንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንና መሰማሪያዋን፥ ዲሞናንና መሰማሪያዋን፥ ነህላልንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። ከሮቤልም ነገድ ቦሶርንና መሰማሪያዋን፥ ያሀጽንና መሰማሪያዋን፥ ቅዴሞትንና መሰማሪያዋን፥ ሜፍዓትንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰማሪያዋን፥ መሃናይምንና መሰማሪያዋን፥ ሐሴቦንንና መሰማሪያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። ከሌዋውያን ወገኖች የቀሩት የሜራሪ ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ ዕጣቸውም ዐሥራ ሁለት ከተማ ነበረ። በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ አርባ ስምንት ከተሞችና መሰማሪያቸው ነበሩ። እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው በዙሪያቸው መሰማሪያዎች ነበራቸው፤ እነዚህም ከተሞች ሁሉ እንዲሁ ነበሩ። ጌታም ለአባቶቻቸው ለመስጠት የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። ጌታም ለአባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፤ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ ማንም ሰው ሊቋቋማቸው አልቻለም፤ ጌታም ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። ጌታ ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።