መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 21:20-45

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 21:20-45 አማ2000

ለቀ​ሩ​ትም ለሌ​ዋ​ው​ያኑ ለቀ​ዓት ልጆች የዕ​ጣ​ቸው ከተ​ሞች ከኤ​ፍ​ሬም ነገድ ደረ​ሱ​አ​ቸው። ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን ሴኬ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጌዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ቄብ​ጻ​ይ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቤቶ​ሮ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። ከዳ​ንም ነገድ ኤል​ቆ​ታ​ይ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ገባ​ቶ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ኤሎ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጌቴ​ራ​ሞ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ጠና​ሕ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዬባ​ታ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሁለ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። የቀ​ሩት የቀ​ዓት ልጆች ወገ​ኖች ከተ​ሞች ሁሉ ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ጋር ዐሥር ናቸው። ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ወገ​ኖች ለጌ​ድ​ሶን ልጆች ከም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ በባ​ሳን ውስጥ የሆ​ነ​ች​ውን ጎላ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቦሶ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሁለ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። ከይ​ሳ​ኮ​ርም ነገድ ቂሶ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዳብ​ራ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሬማ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዓይ​ን​ጋ​ኒ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። ከአ​ሴ​ርም ነገድ መሴ​ላ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ አቤ​ዶ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ሔል​ቃ​ት​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ረዓ​ብ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱ​ንም ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን በገ​ሊላ ውስጥ ቃዴ​ስ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኤማ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃር​ቴ​ን​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፤ ሦስ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። የጌ​ድ​ሶን ልጆች ከተ​ሞች ሁሉ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞች ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ጋር ናቸው። ከሌ​ዋ​ው​ያን ለቀ​ሩት ለሜ​ራሪ ልጆች ወገን ከዛ​ብ​ሎን ነገድ ዮቅ​ና​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃዴ​ስ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዲም​ና​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ሴላ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ። በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል ከሮ​ቤል ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ በሚ​ሶን ምድረ በዳ ቦሶ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኢያ​ዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ቄዴ​ሞ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ሜፍ​ዐ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ። ከጋ​ድም ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን በገ​ለ​ዓድ ውስጥ ራሞ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃሚ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሐሴ​ቦ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኢያ​ዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ። ከሌዊ ወገ​ኖች የቀ​ሩት የሜ​ራሪ ልጆች ከተ​ሞች ሁሉ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ነበሩ፤ ዕጣ​ቸ​ውም ዐሥራ ሁለት ከተማ ነበረ። በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት መካ​ከል የነ​በ​ሩት የሌ​ዋ​ው​ያን ከተ​ሞች ሁሉ በእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች ዙሪያ ካሉ ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር አርባ ስም​ንት ከተ​ሞች ነበሩ። እነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ጋር ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች ሁሉ እን​ዲሁ ነበሩ። [ኢያ​ሱም በየ​ድ​ን​በ​ሮ​ቻ​ቸው ምድ​ርን ማካ​ፈ​ልን ጨረሰ። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ለኢ​ያሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ድር​ሻ​ውን ሰጡት፤ እርሱ የሚ​ፈ​ል​ጋ​ትን ከተማ በኤ​ፍ​ሬም ተራራ የም​ት​ገ​ኘ​ውን ቴም​ና​ሴ​ራን ሰጡት፤ ከተ​ማም ሠራ​ባት፤ በው​ስ​ጧም ተቀ​መጠ። ኢያ​ሱም በም​ደረ በዳ በመ​ን​ገድ የተ​ወ​ለ​ዱ​ትን የገ​ረ​ዘ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ባል​ጩ​ቶች ወስዶ በቴ​ም​ና​ሴራ አኖ​ራ​ቸው።] እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰጠ፤ ወረ​ሱ​አ​ትም፥ ተቀ​መ​ጡ​ባ​ትም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እንደ ማለ​ላ​ቸው በዙ​ሪ​ያ​ቸው ካሉት አሳ​ረ​ፋ​ቸው፤ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ይቋ​ቋ​ማ​ቸው ዘንድ ማንም ሰው አል​ቻ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከተ​ና​ገ​ረው መል​ካም ነገር ሁሉ ተፈ​ጸመ እንጂ ምንም አል​ቀ​ረም።