ኢዮብ 11:13-15
ኢዮብ 11:13-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አንተ ልብህን ንጹሕ ብታደርግ፥ እጆችህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፥ በእጆችህ በደል ቢኖር ካንተ አርቀው፤ በልብህም ኀጢአት አይኑር፤ በዚያን ጊዜ ፊትህ በንጹሕ ውኃ እንደ ታጠበ ያበራል፥ መተዳደፍህንም ታስወግዳለህ፥ አትፈራምም።
ያጋሩ
ኢዮብ 11 ያንብቡኢዮብ 11:13-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ነገር ግን ልብህን ብትሰጠው፣ እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፣ በእጅህ ያለውን ኀጢአት ብታርቅ፣ ክፋትም በድንኳንህ እንዳይኖር ብታደርግ፣ በዚያ ጊዜ ሳታፍር ቀና ትላለህ፤ ያለ ፍርሀት ጸንተህ ትቆማለህ፤
ያጋሩ
ኢዮብ 11 ያንብቡኢዮብ 11:13-15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በእጅህ በደል ቢኖር አርቀው፥ በድንኳንህም ኃጢአት አይኑር፥ አንተ ልብህን ቅን ብታደርግ፥ እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፥ በዚያን ጊዜ በእውነት ፊትህን ያለ ነውር ታነሣለህ፥ ትበረታለህ፥ አትፈራምም።
ያጋሩ
ኢዮብ 11 ያንብቡ