ኢሳይያስ 2:1-15

ኢሳይያስ 2:1-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ስለ ይሁ​ዳና ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አሞፅ ልጅ ወደ ኢሳ​ይ​ያስ የመጣ ቃል። በኋላ ዘመን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በተ​ራ​ሮች ራስ ላይ ይታ​ያል፤ ከኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አሕ​ዛ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ይመ​ጣሉ። ሕግ ከጽ​ዮን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይወ​ጣ​ልና ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ መጥ​ተው፥ “ኑ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ፥ ወደ ያዕ​ቆብ አም​ላክ ቤት እን​ውጣ፤ እር​ሱም መን​ገ​ዱን ያስ​ተ​ም​ረ​ናል፤ በጎ​ዳ​ና​ውም እን​ሄ​ዳ​ለን” ይላሉ። በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ይፈ​ር​ዳል፤ ብዙ አሕ​ዛ​ብ​ንም ይዘ​ል​ፋ​ቸ​ዋል፤ ሰይ​ፋ​ቸ​ው​ንም ማረሻ፥ ጦራ​ቸ​ው​ንም ማጭድ ለማ​ድ​ረግ ይቀ​ጠ​ቅ​ጣሉ፤ ሕዝ​ብም በሕ​ዝብ ላይ ሰይ​ፍን አያ​ነ​ሣም፤ ሰል​ፍ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ማ​ሩም። አሁ​ንም የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ፥ ኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብር​ሃን እን​መ​ላ​ለስ። ሕዝ​ቡን የያ​ዕ​ቆ​ብን ቤት ትቶ​አ​ልና፤ ምድ​ራ​ቸው እንደ ቀድ​ሞው እንደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ምድር በሟ​ርት ተሞ​ል​ቶ​አ​ልና፤ እንደ ባዕድ ልጆ​ችም ሆነ​ዋ​ልና፤ ብዙ እን​ግ​ዶች ልጆ​ችም ተወ​ል​ደ​ው​ላ​ቸ​ዋ​ልና። ምድ​ራ​ቸ​ውም በብ​ርና በወ​ርቅ ተሞ​ል​ታ​ለች፤ ለመ​ዛ​ግ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቍጥር የለ​ውም፤ ምድ​ራ​ቸ​ውም ደግሞ በፈ​ረ​ሶች ተሞ​ል​ታ​ለች፤ ለሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ቍጥር የለ​ውም። ምድ​ራ​ቸ​ውም በእ​ጆ​ቻ​ቸው በሠ​ሩ​አ​ቸው ጣዖ​ታት ተሞ​ል​ታ​ለች፤ በጣ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ለሠ​ሩ​አ​ቸው ይሰ​ግ​ዳሉ። ታና​ሹም ሰው ዝቅ ብሎ​አል፤ ታላ​ቁም ሰው ተዋ​ር​ዶ​አል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይቅር አል​ላ​ቸ​ውም። አሁ​ንም ምድ​ርን ያነ​ዋ​ው​ጣት ዘንድ በተ​ነሣ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ፍ​ራ​ትና ከግ​ር​ማው ክብር የተ​ነሣ ወደ ድን​ጋይ ዋሻ ግቡ፤ በመ​ሬት ውስ​ጥም ተሸ​ሸጉ። የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞች ሰዎች ዐይ​ኖች ይዋ​ረ​ዳሉ፤ የሰ​ዎ​ችም ኵራት ትወ​ድ​ቃ​ለች፥ በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል። የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በት​ዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውና በኵ​ራ​ተ​ኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለ​ውም ላይ ይሆ​ናል፤ እነ​ር​ሱም ይዋ​ረ​ዳሉ፤ ደግ​ሞም በረ​ጅሙ ከፍ ባለ​ውም በሊ​ባ​ኖስ ዝግባ ሁሉ ላይ፥ በባ​ሳ​ንም ዛፍ ሁሉ ላይ፥ በረ​ጅ​ሙም ተራራ ሁሉ ላይ፥ ከፍ ባለ​ውም ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥ በረ​ጅ​ሙም ግንብ ሁሉ ላይ፥ በተ​መ​ሸ​ገ​ውም ቅጥር ሁሉ ላይ፥

ኢሳይያስ 2:1-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ይህ ነው፤ በዘመኑም ፍጻሜ፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራ ከተራሮች ከፍ ብሎ ይመሠረታል፤ ከኰረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ወደዚያ ይጐርፋሉ። ብዙ አሕዛብ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ በጐዳናውም እንድንሄድ፤ መንገዱን ያስተምረናል።” ሕግ ከጽዮን፣ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና። እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል። እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ፣ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ። ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም። እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ ኑ፤ በእግዚአብሔር ብርሃን እንመላለስ። እግዚአብሔር የያዕቆብ ቤት የሆነውን ሕዝብህን ትተሃል፤ እነርሱ በምሥራቅ ሰዎች ከንቱ አምልኮ ተሞልተዋልና፤ እንደ ፍልስጥኤማውያን ያሟርታሉ፤ ከባዕዳን ጋራ አገና ይማታሉ። ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፤ ሀብታቸውም ልክ የለውም። ምድራቸው በፈረሶች ተሞልታለች፤ የሠረገሎቻቸውም ብዛት ልክ የለውም። ምድራቸው በጣዖታት ተሞልታለች፤ ጣቶቻቸው ላበጇቸው፣ ለእጆቻቸው ሥራ ይሰግዳሉ። ሰው ዝቅ ብሏል፤ የሰው ልጅም ተዋርዷል፤ ስለዚህ በደላቸውን ይቅር አትበል። ከእግዚአብሔር አስፈሪነትና ከግርማው ሽሽ፤ ወደ ዐለቶች ሂድ፤ በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ። የእብሪተኛ ሰው ዐይን ይሰበራል፤ የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፤ በዚያ ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል። የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እብሪተኛውንና ትዕቢተኛውን ሁሉ፣ የተኵራራውን በሙሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው። ረዥምና ከፍ ከፍ ያሉትን የሊባኖስ ዝግባዎች ሁሉ፣ የባሳንን የወርካ ዛፎች ሁሉ፣ ታላላቁን ተራራ ሁሉ፣ ከፍ ያለውን ኰረብታ ሁሉ፣ ረዣዥሙን ግንብ ሁሉ፣ የተመሸገውን ቅጥር ሁሉ፣

ኢሳይያስ 2:1-15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ቃል። በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ። ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፥ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ ወደ ጎዳናውም እንሄዳለን ይላሉ። በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፥ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል፥ ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፥ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሳም፥ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም። እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ኑ፥ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ። ሕዝብህን የያዕቆብን ቤት ትተሃልና፥ ይኸውም የምሥራቅን ሰዎች አመል ስለ ተሞሉ፥ እንደ ፍልስጥኤማውያንም ምዋርተኞች ስለ ሆኑ፥ ከባዕድ ልጆችም ጋር ስለ ተባበሩ ነው። ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፥ ለመዛግብቶቻቸውም ፍጻሜ የለውም፥ ምድራቸውም ደግሞ በፈረሶች ተሞልታለች፥ ለሠረገሎቻቸውም ፍጻሜ የለውም። ምድራቸው ደግሞ በጣዖታት ተሞልታለች፥ ጣቶቻቸውም ላደረጉት ለእጃቸው ሥራ ይሰግዳሉ። ታናሹም ሰው ዝቅ ብሎአል፥ ጨዋውም ተዋርዶአል፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር አትበላቸው። ከእግዚአብሔር ማስደንገጥና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻ ግባ፥ በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ። ከፍ ያለችውም የሰው ዓይን ትዋረዳለች፥ የሰዎችም ኵራት ትወድቃለች፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፥ እርሱም ይዋረዳል፥ ደግሞም በረጅሙ ከፍ ባለው በሊባኖስ ዝግባ ሁሉ ላይ፥ በባሳንም ዛፍ ሁሉ ላይ፥ በረጅሙም ተራራ ሁሉ ላይ፥ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ ላይ፥ በረጅሙም ግንብ ሁሉ ላይ፥ በተመሸገውም ቅጥር ሁሉ ላይ፥

ኢሳይያስ 2:1-15 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳ አገርና ስለ ኢየሩሳሌም ከተማ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የተሠራበት ተራራ ከሌሎች ተራራዎች ሁሉ በልጦ ይታያል፤ ከኰረብቶችም ሁሉ እጅግ ከፍ ይላል፤ የብዙ መንግሥታት ሕዝቦች ወደ እርሱ ይጐርፋሉ። ስለዚህ ብዙ ሕዝቦች እንዲህ ይላሉ፦ “ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ስለሚገኝ ኑ ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤተ መቅደስም እንሂድ፤ እርሱ ፈቃዱን እንድናደርግ ያስተምረናል፤ እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን።” እርሱ በብዙ መንግሥታት መካከል በመፍረድ አለመግባባትን ያስወግዳል፤ ስለዚህም ሰይፋቸውን ወደ ማረሻ፥ ጦራቸውንም ወደ ማጭድ ይለውጣሉ፤ መንግሥት በመንግሥት ላይ ጦርነት አያነሣም፤ ከዚያም በኋላ የጦር ትምህርት የሚማር አይኖርም። እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ! ኑ! በእግዚአብሔር ብርሃን እንመላለስ! አምላክ ሆይ! የያዕቆብ ዘሮች የሆኑ ሕዝብህን እርግፍ አድርገህ ትተሃል፤ ምድሪቱ በምሥራቅ አገር ሰዎች ጥንቈላና በፍልስጥኤማውያን ሟርት ተሞልታለች፤ ሕዝቡም ከአሕዛብ ጋር ተባብረዋል። ምድራቸው በብርና በወርቅ ስለ ተሞላች፥ ሀብታቸው ከመጠን በላይ ነው፤ አገራቸው በፈረሶች የተሞላች ሆናለች፤ ሠረገሎቻቸውም እጅግ ብዙ ናቸው። ከዚህም ጋር ምድራቸው በጣዖት የተሞላች ሆናለች፤ በገዛ እጃቸውም ለሠሩት ምስል ይሰግዳሉ። ከዚህም የተነሣ በሁሉም ላይ ኀፍረትና ውርደት ይደርስባቸዋል፤ ጌታ ሆይ! በደላቸውን ይቅር አትበል! ከእግዚአብሔር ቊጣና ከአስፈሪ ግርማው ለማምለጥ በአለት ስንጣቂ ዋሻና በመሬት ጒድጓድ ውስጥ ተሸሸጉ! ትዕቢተኞች ይዋረዳሉ፤ ኩራተኞችም ይቀላሉ፤ እግዚአብሔር ብቻ በክብር ከፍ ከፍ ይላል፤ የሠራዊት አምላክ ትዕቢተኞችና ኩራተኞች የሚዋረዱበትን ቀን ወስኖአል። እርሱ ታላላቅ የሊባኖስ ዛፎችንና የባሳን የወርካ ዛፎችን ያጠፋል። ታላላቅ ተራራዎችንና ኰረብቶችን ዝቅ በማድረግ ደልዳላ ቦታ ያደርጋቸዋል። ረጃጅም የከተማ መጠበቂያ ግንቦችንና የጦር ምሽጎችን ሁሉ ዝቅ ያደርጋል፤

ኢሳይያስ 2:1-15 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ይህ ነው፤ በዘመኑም ፍጻሜ፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራ ከተራሮች ከፍ ብሎ ይመሠረታል፤ ኰረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላሉ፤ ሕዝቦችም ሁሉ ወደዚያ ይጎርፋሉ። ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ ጌታ ተራራ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና። እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል። እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ። ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም። እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ ኑ፤ በጌታ ብርሃን እንመላለስ። የያዕቆብ ቤት የሆነውን፤ ሕዝብህን ትተሃል፤ እነርሱ በምሥራቅ ሰዎች ከንቱ አምልኮ ተሞልተዋልና፤ እንደ ፍልስጥኤማውያን ያሟርታሉ፤ ከባዕዳን ጋር ተባብረዋል። ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፤ ሀብታቸውም ልክ የለውም። ምድራቸው በፈረሶች ተሞልታለች፤ የሠረገሎቻቸውም ብዛት ልክ የለውም። ምድራቸው በጣዖታት ተሞልታለች፤ ጣቶቻቸው ላበጇቸው፤ ለእጆቻቸው ሥራ ይሰግዳሉ። ሰው ዝቅ ብሏል፤ የሰው ልጅም ተዋርዶአል፤ ስለዚህ በደላቸውን ይቅር አትበል። ከጌታ አስፈሪነት ከግርማው ሽሽ፤ ወደ ዐለቶች ሂድ፤ በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ። የእብሪተኛ ሰው ዐይን ይሰበራል፤ የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፤ በዚያን ቀን ጌታ ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እብሪተኛውንና ትዕቢተኛውን ሁሉ፤ የተኩራራውን በሙሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው። ረዥምና ከፍ ከፍ ያሉትን የሊባኖስ ዝግባዎች ሁሉ፤ የባሳንን የወርካ ዛፎች ሁሉ፤ ታላላቁን ተራራ ሁሉ፤ ከፍ ያለው ኮረብታ ሁሉ፤ ረጃጅሙን ግንብ ሁሉ፤ የተመሸገውን ቅጥር ሁሉ፤