ዘፍጥረት 31:2-21
ዘፍጥረት 31:2-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የላባ አመለካከት ከቀድሞው የተለወጠበት መሆኑንም ያዕቆብ ተረዳ። እግዚአብሔርም ያዕቆብን፣ “ወደ አባቶችህና ዘመዶችህ አገር ተመለስ፤ እኔም ካንተ ጋራ እሆናለሁ” አለው። ስለዚህም ያዕቆብ መንጎቹ ወደ ተሰማሩበት መስክ እንዲመጡ፣ ራሔልንና ልያን አስጠራቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ “አባታችሁ ስለ እኔ ያለው አመለካከት እንደ ቀድሞው አለመሆኑን ተረድቻለሁ፤ ቢሆንም የአባቴ አምላክ አልተለየኝም፤ መቼም ባለኝ ዐቅም አባታችሁን ማገልገሌ ከእናንተ የተሰወረ አይደለም። አባታችሁ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ እየለዋወጠ አታልሎኛል፣ ሆኖም እንዲጐዳኝ እግዚአብሔር አልፈቀደለትም። እርሱ፣ ‘ደመወዝህ ዝንጕርጕሮቹ ይሆናሉ’ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ዝንጕርጕር ወለዱ፤ ደግሞም ‘ደመወዝህ ሽመልመሌዎቹ ይሆናሉ’ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መልክ ያላቸውን ወለዱ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የአባታችሁን ከብቶች ወስዶ ለእኔ ሰጠኝ። “እንስሳቱ በሚጠቁበት ወራት፣ የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች መልካቸው፣ ሽመልመሌ፣ ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸው መሆናቸውን ዐይኔን አንሥቼ በሕልሜ አየሁ። የእግዚአብሔርም መልአክ፣ ‘ያዕቆብ’ አለኝ፤ እኔም፣ ‘እነሆ አለሁኝ’ አልሁት። እርሱም ‘መንጎቹን የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች ሁሉ ሽመልመሌ መልክ ያላቸው፣ ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸው መሆናቸውን ቀና ብለህ ተመልከት፤ ላባ በአንተ ላይ የሚፈጽመውን ድርጊት ሁሉ አይቻለሁና፤ የድንጋይ ሐውልት በማቆም ዘይት ቀብተህ የተሳልህባት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፤ አሁንም ይህን አገር ፈጥነህ ልቀቅና ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመልሰህ ሂድ’ አለኝ።” ራሔልና ልያም እንዲህ ብለው መለሱለት፤ “ከአባታችን ሀብት የምናገኘው ምን ውርስ አለ? እኛን የሚያየን እንደ ባዕድ አይደለምን? ደግሞም እኮ እኛን ሸጦናል፤ የተሸጥንበትንም ዋጋ ራሱ በልቶታል። እግዚአብሔር ከአባታችን ወስዶ ለአንተ የሰጠው ሀብት ሁሉ የእኛና የልጆቻችን ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የነገረህን ሁሉ አድርግ።” ከዚያም ያዕቆብ ልጆቹንና ሚስቶቹን ግመሎች ላይ አስቀመጠ፤ በመስጴጦምያ ካፈራው ሀብት ሁሉ ጋራ ከብቶቹን በሙሉ ወደ ፊት አስቀደመ፤ ወደ አባቱም ወደ ይሥሐቅ አገር፣ ወደ ከነዓን ምድር ጕዞውን ቀጠለ። ላባ በጎቹን ሊሸልት ሄዶ ሳለ፣ ራሔል የአባቷን ቤት የጣዖታት ምስል ሰረቀች። ያዕቆብም ቢሆን፣ መኰብለሉን ለሶርያዊው ለላባ ሳይገልጥለት በመቅረቱ አታልሎታል። ያዕቆብ የርሱ የሆነውን ሁሉ ይዞ፣ የኤፍራጥስን ወንዝ ተሻግሮ ወደ ኰረብታማው አገር፣ ወደ ገለዓድ አመራ።
ዘፍጥረት 31:2-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ያዕቆብም የላባን ፊት አየ፤ እነሆም፥ ከእርሱ ጋር እንደ ዱሮው አልሆነም። እግዚአብሔርም ያዕቆብን፥ “ወደ አባትህና ወደ ዘመዶችህ ሀገር ተመለስ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ” አለው። ያዕቆብም ልኮ ራሔልንና ልያን ወደ በጎቹ መሰማሪያ ወደ ሜዳ ጠራቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “እነሆ፥ የአባታችሁ ፊት እንደ ዱሮ ከእኔ ጋር እንዳልሆነ አያለሁ፤ ነገር ግን የአባቴ አምላክ ከእኔ ጋር ነው። እኔ ባለኝ ጕልበቴ ሁሉ አባታችሁን እንዳገለገልሁ ታውቃላችሁ። አባታችሁ ግን አሳዘነኝ፥ ደመወዜንም ዐሥር ጊዜ ለወጠ፤ እግዚአብሔር ግን ክፉን ያደርግብኝ ዘንድ አልፈቀደለትም። ደመወዝህ ዝንጕርጕሮቹ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ዝንጕርጕሮችን ወለዱ፤ ነጫጮቹ ደመወዝህ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ነጫጮችን ወለዱ። እግዚአብሔርም የአባታችሁን በጎች ሁሉ ነሥቶ ለእኔ ሰጠኝ። እንዲህም ሆነ፤ በጎቹ በሚፀንሱ ጊዜ ዐይኔን አንሥቼ በሕልም አየሁ፤ እነሆም፥ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ነጭ፥ ዝንጕርጕሮችና ሐመደ ክቦ ነበሩ። እግዚአብሔርም በሕልም፦ ‘ያዕቆብ ያዕቆብ’ አለኝ፤ እኔም፦ ‘እነሆኝ ምንድን ነው?’ አልሁት። እንዲህም አለኝ፦ ዐይንህን አቅንተህ እይ፤ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ነጭ፥ ሐመደ ክቦና ዝንጕርጕሮች ናቸው፤ ላባ በአንተ ላይ የሚያደርገውን አይቻለሁና። ሐውልቱን ዘይት በቀባህባት፥ በዚያች ለእኔ ስእለት በተሳልህባት ሀገር የተገለጥሁልህ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። አሁንም ተነሥተህ ከዚህ ሀገር ውጣ፤ ወደ ተወለድህባትም ምድር ተመለስ፤ እኔም ከአንተ ጋር እኖራለሁ።” ራሔልና ልያም መልሰው እንዲህ አሉት፥ “በአባታችን ቤት ለእኛ ድርሻ ወይም ርስት በውኑ አለን? እኛ በእርሱ ዘንድ እንደ ባዕድ የተቈጠርን አይደለምን? እርሱ እኛን ሽጦ ዋጋችንን በልቶአልና። ስለዚህም እግዚአብሔር ከአባታችን የነሣው ይህ ሁሉ ሀብትና ክብር ለእኛና ለልጆቻችን ነው፤ አሁንም እግዚአብሔር ያለህን ሁሉ አድርግ።” ያዕቆብም ተነሣ፤ ልጆቹንና ሚስቶቹንም በግመሎች ላይ አስቀመጠ። መንጎቹንም ሁሉ፥ የቤቱንም ዕቃ ሁሉ፥ በሁለቱ ወንዞች መካከል ሳለ ያገኛቸውን ከብቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ ከነዓን ምድር ሄደ። ላባ ግን በጎቹን ለመሸለት ሄዶ ነበር፤ ራሔልም የአባቷን ጣዖቶች ሰረቀች። ያዕቆብም ነገሩን ከሶርያዊው ከላባ ሰወረ፤ እንደሚሄድም አልነገረውም። እርሱም ያለውን ሁሉ ይዞ ኰበለለ፤ ተነሥቶም ወንዙን ተሻገረ፤ በገለዓድ ተራራም አደረ።
ዘፍጥረት 31:2-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የላባ አመለካከት ከቀድሞው የተለወጠበት መሆኑንም ያዕቆብ ተረዳ። እግዚአብሔርም ያዕቆብን፣ “ወደ አባቶችህና ዘመዶችህ አገር ተመለስ፤ እኔም ካንተ ጋራ እሆናለሁ” አለው። ስለዚህም ያዕቆብ መንጎቹ ወደ ተሰማሩበት መስክ እንዲመጡ፣ ራሔልንና ልያን አስጠራቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ “አባታችሁ ስለ እኔ ያለው አመለካከት እንደ ቀድሞው አለመሆኑን ተረድቻለሁ፤ ቢሆንም የአባቴ አምላክ አልተለየኝም፤ መቼም ባለኝ ዐቅም አባታችሁን ማገልገሌ ከእናንተ የተሰወረ አይደለም። አባታችሁ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ እየለዋወጠ አታልሎኛል፣ ሆኖም እንዲጐዳኝ እግዚአብሔር አልፈቀደለትም። እርሱ፣ ‘ደመወዝህ ዝንጕርጕሮቹ ይሆናሉ’ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ዝንጕርጕር ወለዱ፤ ደግሞም ‘ደመወዝህ ሽመልመሌዎቹ ይሆናሉ’ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መልክ ያላቸውን ወለዱ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የአባታችሁን ከብቶች ወስዶ ለእኔ ሰጠኝ። “እንስሳቱ በሚጠቁበት ወራት፣ የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች መልካቸው፣ ሽመልመሌ፣ ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸው መሆናቸውን ዐይኔን አንሥቼ በሕልሜ አየሁ። የእግዚአብሔርም መልአክ፣ ‘ያዕቆብ’ አለኝ፤ እኔም፣ ‘እነሆ አለሁኝ’ አልሁት። እርሱም ‘መንጎቹን የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች ሁሉ ሽመልመሌ መልክ ያላቸው፣ ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸው መሆናቸውን ቀና ብለህ ተመልከት፤ ላባ በአንተ ላይ የሚፈጽመውን ድርጊት ሁሉ አይቻለሁና፤ የድንጋይ ሐውልት በማቆም ዘይት ቀብተህ የተሳልህባት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፤ አሁንም ይህን አገር ፈጥነህ ልቀቅና ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመልሰህ ሂድ’ አለኝ።” ራሔልና ልያም እንዲህ ብለው መለሱለት፤ “ከአባታችን ሀብት የምናገኘው ምን ውርስ አለ? እኛን የሚያየን እንደ ባዕድ አይደለምን? ደግሞም እኮ እኛን ሸጦናል፤ የተሸጥንበትንም ዋጋ ራሱ በልቶታል። እግዚአብሔር ከአባታችን ወስዶ ለአንተ የሰጠው ሀብት ሁሉ የእኛና የልጆቻችን ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የነገረህን ሁሉ አድርግ።” ከዚያም ያዕቆብ ልጆቹንና ሚስቶቹን ግመሎች ላይ አስቀመጠ፤ በመስጴጦምያ ካፈራው ሀብት ሁሉ ጋራ ከብቶቹን በሙሉ ወደ ፊት አስቀደመ፤ ወደ አባቱም ወደ ይሥሐቅ አገር፣ ወደ ከነዓን ምድር ጕዞውን ቀጠለ። ላባ በጎቹን ሊሸልት ሄዶ ሳለ፣ ራሔል የአባቷን ቤት የጣዖታት ምስል ሰረቀች። ያዕቆብም ቢሆን፣ መኰብለሉን ለሶርያዊው ለላባ ሳይገልጥለት በመቅረቱ አታልሎታል። ያዕቆብ የርሱ የሆነውን ሁሉ ይዞ፣ የኤፍራጥስን ወንዝ ተሻግሮ ወደ ኰረብታማው አገር፣ ወደ ገለዓድ አመራ።
ዘፍጥረት 31:2-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ያዕቆብም የላባን ፊት አየ እነሆም ከእርሱ ጋር እንደ ዱሮው አልሆነም። እግዚአብሔርም ያዕቆብን፦ ወደ አባትህ ምድር ወደ ዘመዶችህም ተመለስ ከአንተም ጋር እሆናለሁ አለው። ያዕቆብም ልኮ ራሔልንና ልያን ወደ በጎቹ ስፍራ ወደ ሜዳ ጠራቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ የአባታችሁ ፊት ከእኔ ጋር እንደ ዱሮ እንዳልሆን አያለሁ ነገር ግን የአባቴ አምላክ ከእኔ ጋር ነው። እኔ ባለኝ ጕልበቴ ሁሉ እንዳገለገልሁ ታውቃላችሁ። አባታችሁ ግን አታለለኝ ደመወዜንም አሥር ጊዜ ለወጠ እግዚአብሔር ግን ክፋን ያደርግብኝ ዘንድ አልፈቀደለትም። ደመወዝህ ዝንጕርጕሮች ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ዝንጕርጕሮችን ወለዱ ሽመልመሌ መሳዮቹ ደመወዝህ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መሳዮችን ወለዱ። እግዚአብሔርም የአባታችሁን በጎቹ ሁሉ ነሥቶ ለእኔ ሰጠኝ እንዲህም ሆነ በጎቹ በጎመጁ ጊዜ ዓይኔን አንሥቼ በሕልም አየሁ እነሆም በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችን የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ነበሩ። የእግዚአብሔርም መልአክ በሕልም፦ ያዕቆብ ሆይ አለኝ እኔም፦ እነሆኝ አልሁት። እንዲህም አለኝ፦ ዓይንህን አቅንተህ እይ በበጎችን በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ናቸው፤ ላባ በአንተ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ አይቼአለሁና። ሐውልት የቀባህበት በዚያም ለእኔ ስእለት የተሳልህበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ አገር ውጣ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመለስ። ራሔልና ልያም መልሰው እንዲህ አሉት፦ በአባታችን ቤት ለእኛ ድርሻና ርስት በውኑ ቀርቶልናልን? እኛ በእርሱ ዘንድ እንደ ባዕድ የተቈጠርን አይደለንምን? እርሱ እኛን ሸጦ ዋጋችንን በልቶአልና። ስለዚህም እግዚአብሔር ከአባታችን የነሣው ይህ ሁሉ ሀብት ለእኛና ለልጆቻችን ነው፤ አሁንም እግዚአብሔር ያለህን ሁሉ አድርግ። ያዕቆብም ተነሣ ልጆቹንና ሚስቶቹንም በግመሎች ላይ አስቀመጠ፤ መንጎቹንም ሁሉ የቤቱንም ዕቃ ሁሉ በሁለት ወንዞች መካከል ሳለ ያገኛቸውን ከብቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ ከነዓን ምድር ሄደ። ላባ ግን በጎቹን ለመሸለት ሄዶ ነበር ራሔልም የአባትዋን ተራፌም ሰረቀም። ያዕቆብም የሶርያውን ሰው ላባን ከድቶ ኮበለለ መኮብለሉን፥ አልነገረውም። እርሱም ያለውን ሁሉ ይዞ ኮበለለ ተነሥቶም ወንዙን ተሻገረ፥ ፊቱንም ወደ ገለዓድ ተራራ አቀና።
ዘፍጥረት 31:2-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በላባም ዘንድ እንደ ቀድሞው ተወዳጅ አለመሆኑን ተረዳ። በዚህን ጊዜ እግዚአብሔር ያዕቆብን “ወደ አባቶችህና ወደ ዘመዶችህ አገር ተመለስ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ” አለው። ስለዚህ ያዕቆብ መንጋዎቹ ወደ ተሰማሩበት መስክ እንዲመጡ ራሔልንና ልያን አስጠራቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ “አባታችሁ እንደ ቀድሞው ጊዜ እንደማይወደኝ ተረድቼአለሁ፤ ነገር ግን የአባቴ አምላክ ከእኔ ጋር አለ፤ ጒልበቴን ሳልቈጥብ በትጋት አባታችሁን እንዳገለገልኩ እናንተም ታውቃላችሁ፤ እርሱ ግን ዐሥር ጊዜ ደመወዜን በመለዋወጥ አታለለኝ፤ ሆኖም እኔን ለመጒዳት እግዚአብሔር አልፈቀደለትም፤ ላባ ‘ዝንጒርጒሮቹ ሁሉ ለአንተ ደመወዝ ይሁኑ’ ባለኝ ጊዜ፥ መንጋዎቹ ሁሉ ዝንጒርጒር ወለዱ፤ ደግሞም ‘ሽመልመሌ መሳዮቹ ሁሉ ለአንተ ደመወዝ ይሁኑ’ ባለኝ ጊዜ፥ መንጋዎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መሳዮች ወለዱ። እግዚአብሔር የአባታችሁን የላባን መንጋዎች ወስዶ ለእኔ የሰጠኝ በዚህ ዐይነት ነው። “እንስሶቹ ለመፅነስ ፍትወት በሚያድርባቸው ወራት የሚያጠቁአቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፥ ዝንጒርጒርና ነቊጣ መሆናቸውን በሕልም አየሁ። በዚያው ሕልም የእግዚአብሔር መልአክ ‘ያዕቆብ!’ ብሎ ጠራኝ፤ እኔም ‘እነሆ፥ አለሁ!’ አልኩ። እርሱም እንዲህ አለኝ፤ ‘መንጋዎቹን የሚያጠቁአቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፥ ዝንጒርጒርና ነቊጣ ያለባቸው መሆናቸውን ተመልከት፤ ላባ የፈጸመብህን በደል ስላየሁ ይህን ያደረግኹት እኔ ነኝ፤ የመታሰቢያ ድንጋይ አቁመህ ዘይት በመቀባት በተሳልክበት ቦታ በቤትኤል የተገለጥኩልህ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ አሁንም ከዚህ አገር በፍጥነት ወጥተህ ወደ ተወለድክበት አገር ተመለስ።’ ” ራሔልና ልያ ለያዕቆብ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ “በአባታችን ቤት የውርስ ድርሻ ቀርቶልናልን? እርሱ እኛን የሚያየን እንደ ባዕድ አይደለምን? አስቀድሞ ሸጦን ነበር፤ አሁን ደግሞ ለእኛ ዋጋ የተከፈለውን ሁሉ አጥፍቶታል፤ አሁንም እግዚአብሔር ከአባታችን ወስዶ ለአንተ የሰጠህ ሀብት ሁሉ የእኛና የልጆቻችን ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ሁሉ አድርግ።” ያዕቆብም ተነሥቶ ልጆቹንና ሚስቶቹን በግመሎች ላይ አስቀመጠ፤ በመስጴጦምያ ሳለ ያገኛቸውን መንጋዎችና ዕቃዎችን ሁሉ ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ሄደ። ላባ በጎች ሊሸልት ሄዶ ስለ ነበር፥ እርሱ በሌለበት ራሔል በቤት የነበሩትን የአባቷን ጣዖቶች ሰርቃ ሄደች። ያዕቆብ መሄዱን ለላባ ሳይገልጥለት አታሎት ሄደ፤ የራሱ የሆነውን ሀብት ይዞ በፍጥነት ተጓዘ፤ የኤፍራጥስንም ወንዝ ተሻግሮ ወደ ኮረብታማው አገር ወደ ገለዓድ ሄደ።
ዘፍጥረት 31:2-21 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እንደ ቀድሞው በላባ ተወዳጅ አለመሆኑን ያዕቆብም አየ። በዚህን ጊዜ ጌታ ያዕቆብን፥ “ወደ አባቶችህ ምድር እና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፥ ከአንተም ጋር እሆናለሁ” አለው። ያዕቆብም ላከና ራሔልንና ልያን በጎቹ ወደ ነበሩበት መስክ ጠራቸው፥ እንዲህም አላቸው፥ “አባታችሁ ከእኔ ጋር እንደ ቀድሞው እንደማይወደኝ አያለሁ፥ ነገር ግን የአባቴ አምላክ ከእኔ ጋር ነው። እኔ ባለኝ ጉልበቴ ሁሉ አባታችሁን እንዳገለገልኩ እናንተም ታውቃላችሁ። አባታችሁ ግን አታለለኝ፥ ደመወዜንም ዐሥር ጊዜ ለወጠ፥ እግዚአብሔር ግን ይጎዳኝ ዘንድ አልፈቀደለትም። ‘ዝንጉርጉሮቹ ሁሉ ለአንተ ደመወዝ ይሁኑ’ ቢለኝ፥ መንጋዎቹ ሁሉ ዝንጉርጉሮችን ወለዱ፤ ደግሞም ‘ሽመልመሌ መሳዮቹ ሁሉ ለአንተ ደመወዝ ይሁኑ’ ቢለኝ፥ መንጋዎቹ ሁሉ ሽመልመሌ ወለዱ። እግዚአብሔርም የአባታችሁን በጎች ሁሉ ነሥቶ ለእኔ ሰጠኝ። በመንጋዎቹ መራቢያ ወራት ዐይኖቼን አነሳሁ፥ በሕልምም በበጎቹ ላይ የሚንጠላጠሉት አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፥ ዝንጉርጉርና ነቊጣ እንደ ነበሩ አየሁ። የእግዚአብሔርም መልአክ በሕልም፦ ያዕቆብ ሆይ አለኝ፥ እኔም፦ እነሆኝ አልሁት። እርሱም እንዲህ አለኝ፥ ‘ዓይንህን አቅናና እይ፥ መንጋዎቹ ላይ የሚንጠላጠሉት ፍየሎች ሁሉ ሽመልመሌ፥ ዝንጉርጉሮች እና ነቊጣ ናቸው፤ላባ በአንተ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ አይቼአለሁና። ሐውልት የቀባህበት እና ለእኔ ስእለት የተሳልህበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፥ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ ምድር ውጣ፥ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመለስ።’” ራሔልና ልያም መልሰው እንዲህ አሉት፥ “በአባታችን ቤት ለእኛ አንዳች ድርሻ ወይም ርስት አለን? እኛ በእርሱ ዘንድ እንደ ባዕድ የተቈጠርን አይደለንምን? እርሱ እኛን ሸጦ ዋጋችንን በልቶአልኮ። ስለዚህም እግዚአብሔር ከአባታችን የነሣው ሀብት ሁሉ የእኛና የልጆቻችን ነው፥ እንግዲያውስ አሁንም፥ እግዚአብሔር ያለህን ሁሉ፥ አድርግ።” ከዚያም ያዕቆብ ተነሣ፥ ልጆቹንና ሚስቶቹንም በግመሎች ላይ አስቀመጠ፤ መንጎቹንም ሁሉ፥ ያፈራውን ንብረት ሁሉ፥ ፓዳን-ኣራም ሳለ ያገኛቸውን ከብቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ ከነዓን ምድር ሄደ። ላባም በጎቹን ለመሸለት ሄዶ ነበር፥ ራሔልም የአባትዋን ቤት ጣዖቶች ሰረቀች። ያዕቆብም ለመሄድ ማቀዱን ሳይነግረው ሶርያዊውን ላባን ከድቶ ኮበለለ። እርሱ ያለውን ሁሉ ይዞ ኮበለለ፥ ተነሥቶም የኤፍራጥስን ወንዝ ተሻገረ፥ ፊቱንም ወደ ኮረብታማው አገር ገለዓድ አቀና።