ዘዳግም 28:44-45 - Compare All Versions

ዘዳግም 28:44-45 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እርሱ ያበድርሃል እንጂ አንተ አታበድረውም። እርሱ ራስ ይሆናል፤ አንተ ግን ጅራት ትሆናለህ። እነዚህ ርግማኖች ሁሉ በአንተ ላይ ይመጣሉ፤ አምላክህን እግዚአብሔርን ስላልታዘዝህና የሰጠህን ትእዛዝና ሥርዐት ስላልጠበቅህ እስክትጠፋ ድረስ ይከተሉሃል፤ ይወርዱብሃልም።

ዘዳግም 28:44-45 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

መጻተኞች ለአንተ ገንዘብ አበዳሪዎች ይሆናሉ፤ አንተ ግን ለእነርሱ የምታበድራቸው ገንዘብ አይኖርህም፤ በመጨረሻም እነርሱ እንደ ራስ መሪ ይሆናሉ፤ አንተ ግን እንደ ጅራት ወደ ኋላ ትቀራለህ። “አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ታዛዥ ሆነህ ስላልተገኘህና እርሱ የሰጠህን ደንቦችና ትእዛዞች ስላልጠበቅህ እነዚህ ሁሉ መቅሠፍቶች ይመጡብሃል፤ ፈጽሞ እስከምትደመሰስ ድረስ ከአንተ አይርቁም፤

ዘዳግም 28:44-45 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እርሱ ያበ​ድ​ር​ሃል፤ አንተ ግን አታ​በ​ድ​ረ​ውም፤ እርሱ ራስ ይሆ​ናል፤ አን​ተም ጅራት ትሆ​ና​ለህ። የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስላ​ል​ሰ​ማህ፥ ያዘ​ዘ​ህ​ንም ትእ​ዛ​ዙ​ንና ሥር​ዐ​ቱን ስላ​ል​ጠ​በ​ቅህ፥ እስ​ክ​ት​ጠፋ ድረስ እነ​ዚህ መር​ገ​ሞች ሁሉ ይወ​ር​ዱ​ብ​ሃል፤ ያሳ​ድ​ዱ​ህ​ማል፤ ያገ​ኙ​ህ​ማል።

ዘዳግም 28:44-45 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እርሱ ያበድርሃል፥ አንተ ግን አታበድረውም፤ እርሱ ራስ ይሆናል፥ አንተም ጅራት ትሆናለህ። የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ስላልሰማህ፥ ያዘዘህንም ትእዛዙንና ሥርዓቱን ስላልጠበቅህ፥ እስክትጠፋ ድረስ እነዚህ መርገሞች ሁሉ ይወርዱብሃል፥ ያሳድዱህማል፥ ያገኙህማል።

ዘዳግም 28:44-45 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እርሱ ያበድርሃል፤ አንተም ትበደረዋለህ። እርሱ ራስ ይሆናል፤ አንተ ግን ጅራት ትሆናለህ። “ጌታ እግዚአብሔርን ስላልታዘዝህና የሰጠህን ትእዛዝና ሥርዓት ስላልጠበቅህ እነዚህ ርግማኖች ሁሉ በአንተ ላይ ይመጣሉ፥ እስክትጠፋ ድረስ ያሳድዱህማል፥ ይወርሱሃል።