የማቴዎስ ወንጌል 8:23-26

የማቴዎስ ወንጌል 8:23-26 አማ54

ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት። እነሆም ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፦ ጌታ ሆይ፥ አድነን፥ ጠፋን እያሉ አስነሡት። እርሱም፦ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ ስለ ምን ትፈራላችሁ? አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፥ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች