መጽሐፈ ኢያሱ 9:3-6

መጽሐፈ ኢያሱ 9:3-6 አማ54

የገባዖን ሰዎች ግን ኢያሱ በኢያሪኮና በጋይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፥ እነርሱ ደግሞ ተንኰል አደረጉ፥ ለራሳቸውም ስንቅ ያዙ፥ በአህዮቻቸውም ላይ አሮጌ ዓይበትና ያረጀና የተቀደደ የተጠቀመም የጠጅ አቁማዳ ጫኑ። ያረጀ የተጠቀመም ጫማ በእግራቸው አደረጉ አሮጌም ልብስ ለበሱ፥ ለስንቅም የያዙት እንጀራ ሁሉ የደረቀና የሻገተ ነበረ። ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ሄደው ለእርሱና ለእስራኤል ሰዎች፦ ከሩቅ አገር መጥተናል፥ አሁንም ከእኛ ጋር ኪዳን አድርጉ አሉ።