መጽሐፈ ኢያሱ 14:6-9

መጽሐፈ ኢያሱ 14:6-9 አማ54

የይሁዳም ልጆች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፥ ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ አለው፦ ለአምላክ ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግዚአብሔር በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ነገር ታውቃለህ። የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ምድርን እሰልል ዘንድ ከቃዴስ በርኔ በላከኝ ጊዜ እኔ የአርባ ዓመት ሰው ነበርሁ እኔም በልቤ የነበረውን ቃል መለስሁለት። ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞቼ ግን የሕዝቡን ልብ አቀለጡ፥ እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሜ ተከተልሁ። ሙሴም በዚያ ቀን፦ አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽመህ ተከትለሃልና እግርህ የረገጠው ምድር ለአንተና ለልጆችህ ለዘላለም በእርግጥ ርስት ይሆናል ብሎ ማለ።