ትንቢተ ኢሳይያስ 7:13-16

ትንቢተ ኢሳይያስ 7:13-16 አማ54

እርሱም አለ፦ እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፥ ስሙ፥ በውኑ ሰውን ማድከማችሁ ቀላል ነውን? አምላኬን ደግሞ የምታደክሙ፥ ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፥ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ክፉን ለመጥላት መልካሙንም ለመምረጥ ሲያውቅ ቅቤና ማር ይበላል። ሕፃኑም ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት አገር ባድማ ትሆናለች።