ኦሪት ዘፍጥረት 9:1-7

ኦሪት ዘፍጥረት 9:1-7 አማ54

እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው እንዲህም አላቸው፤ ብዙ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት። አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭታችሁ በምድር አራዊት፥ በሰማይም ወፎች፥ በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱትም፥ በባሕር ዓሦችም ሁሉ ላይ ይሁን እነርሱም በእጃችሁ ተሰጥተዋል። ሕይወት ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ መብል ይሁናችሁ ሁሉን እንደ ለመለመ ቡቃያ ሰጠኍችሁ። ነገር ግን ነፍሱ ደሙ ያለችበትን ሥጋ አትብሉ፥ ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ እሻዋለሁ፥ ከአራዊት ሁሉ እጅ እሻዋለሁ ከስውም እጅ ከስው ወንድም እጅ፤ የስውን ነፍስ እሻለሁ። የስውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ ደሙ ይፈስሳል ሰውን በእግዚአብሔር መልክ ፈጥሮታልና። እናንተም ብዙ ተባዙ በምድር ላይ ተዋለዱ፥ እርቡባትም።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}