እስራኤልም ለእርሱ ያለውን ሁሉ ይዞ ተነሣ ወደ ቤርሳቤህ መጣ መሥዋዕትንም ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ ሠዋ። እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ፦ ያዕቆብ ያዕቆብ ብሎ ለእስራኤል ተናገረው። እርሱም፦ እነሆኝ አለ። አለውም፦ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ ወደ ግብፅ መውረድ አትፍራ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና። እኔ ወደ ግብፅ አብሬህ እወርዳለሁ ከዚያንም ደግሞ እኔ አወጣሃለሁ፤ ዮሴፍም እጁን በዓይንህ ላይ ያኖራል። ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ተነሣ የእስራኤልም ልጆች ያዕቆብም ልጆች ያዕቆብን ይወስዱ ዘንድ ፈርዖን በሰደዳቸው ሰረገሎች አባታቸውን ያዕቆብንና ሕፃናቶቻቸውንም ሴቶቻቸውንም ወሰዱ። እንስሶቻቸውንም በከነዓን አገርም ያገኙትን ከብታቸውን ሁሉ ይዘው ያዕቆብ ዘሩ ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ መጡ ወንዶች ልጆቹንና የልጆቹን ወንዶች ልጆች ሴቶች ልጆቹንና የወንዶች ልጆቹን ሴቶች ልጆች ዘሩንም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ አስገባቸው። ወደ ግብፅም የገቡት የእስራኤል ልጆች ስም ይህ ነው ያዕቆብና ልጆቹ የያዕቆብ በኵር ሮቤል። የሮቤልም ልጆች ሄኖኅ ፈሉሶ፥ አስሮን፥ ከርሚ። የስሞዖን ልጆች ይሙኤል ያሚን፥ አሃድ ያኪን ጾሐር፥ የከነዓናዊት ልጅ ሳኡል። የሌዊም ልጆች ጌድሶን፥ ቀዓት ሜራሪ። የይሁዳም ልጆች ዔር አውናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ፤ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ የፋሬስም ልጆች ኤስሮችም ሐሙል። የይሳኮር ልጆች ቶላ፥ ፋዋ፥ ዮብ ሺምሮን። የዛብሎንም ልጆች ሴሬድ ኤሎን ያሕልኤል። ልያ በመስዼጦምያ በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነዚህ ናቸው ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ዲና እነዚን ናቸው ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ ሦስት ነፍስ ናቸው። የጋድም ልጆች ጽፎን፥ ሐጊ፥ ሹኒ ኤስቦን፥ ዔሪ አሮዲ አርኤሊ የአሲርም ልጆች ዪምና የሱዋ፥ የሱዊ በሪዓ እኅታቸው ሤራሕ የበሪዓ ልጆችም ሔቤር መልኪኤል። ላባ ለልጁ ለልያ የሰጣት የዘለፋ ልጆች እነዚህ ናቸው እነዚህን አሥራ ስድስቱንም ነፍስ ለያዕቆብ ወለደች። የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች ዮሴፍና ብንያም ናቸው። ለዮሴፍም በግብፅ ምድር ምነሴና ኤፍሬም ተወለዱለት የሄልዮቱ ከተማ ካህን የዾጥፌራ ልጅ አስናት የወለደቻቸው ናቸው። የብንያም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ አስቤል የቤላ ልጆችም ጌራ ናዕማን አኪ ሮስ፥ ማንፌን፥ ሑፊም ጌራም አርድን ወለደ። ለያዕቆብ የተወለዱለት የራሔልም ልጆች እነዚህ ናቸው ሁሉም አሥራ አራት ነፍስ ናቸው። የዳንም ልጆች ሑሺም የንፍታሌምም ልጆች ያሕጽኤል ጊኑ ዮጽር፥ ሺሌም። ላባ ለልጁ ለራሔል የሰጣት የባላ ልጆች እነዚህ ናቸው እነዚህንም ለያዕቆብ ወለደችለት ሁሉም ሰባት ነፍስ ናቸው። ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት ሰዎች ሁሉ ከጉልበቱ የወጡት ከልጆቹ ሚስቶች ሌላ ሁላቸው ስድሳ ስድስት ናቸው። በግብፅ ምድር የተወለዳለት የዮሴፍም ልጆች ሁለት ናቸኤ ወደ ግብፅ የገቡት የያዕቆብ ቤተስዎች ሁሉ ሰባ ናቸው።
ኦሪት ዘፍጥረት 46 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 46:1-27
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች