ኦሪት ዘፍጥረት 26:12-16

ኦሪት ዘፍጥረት 26:12-16 አማ54

ይስሐቅም በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፥ በዚያች ዓመትም መቶ እጥፍ አገኘ እግዚአብሔርም ባረከው። ባለ ጠጋ ሰውም ሆነ እጅግ እስኪበልጥ ድረስም እየጨመተ ይበዛ ነበር፤ የበግና የላም ከብትም ሎሌዎችም እጅግ በዙለት የፍልስጥኤም ሰዎች ቀኑበት። በአባቱ በአብርሃም ዘመን የአባቱ ሎሌዎች የማሱአቸውን ጕድጓዶች ሁሉ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፈኑአቸው አፈርንም ሞሉባቸው። አቢሜሌክም ይስሐቅን፦ ከእኛ ተለይተህ ሂድ ከእኛ ይልቅ እጅግ በርትተሃልና አለው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}