ትንቢተ ሕዝቅኤል 28:15-17

ትንቢተ ሕዝቅኤል 28:15-17 አማ54

ከተፈጠርህበት ቀን ጀምረህ በደል እስኪገኝብህ ድረስ በመንገድህ ፍጹም ነበርህ። በንግድህ ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ ኃጢአትንም ሠራህ፥ ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፥ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፥ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ። በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፥ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፥ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ።