ጸሎትዋንም በእግዚአብሔር ፊት ባበዛች ጊዜ ዔሊ አፍዋን ይመለከት ነበር። ሐናም በልብዋ ትናገር ነበር፥ ድምፅዋም ሳይሰማ ከንፈርዋን ታንቀሳቅስ ነበር፥ ዔሊም እንደ ሰከረች ቈጠራት። ዔሊም፦ ስካርሽ እስከ መቼ ነው? የወይን ጠጅሽን ከአንቺ አርቂው አላት። ሐናም፦ ጌታዬ ሆይ፥ አይደለም፥ እኔስ ልብዋ ያዘነባት ሴት ነኝ፥ ጠጅና ሌላ የሚያሰክር ነገር አልጠጣሁም፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ነፍሴን አፈሰስሁ፥ ኀዘኔና ጭንቀቴ ስለ በዛ እስከ አሁን ድረስ ተናግሬአለሁና ባሪያህን እንደ ምናምንቴ ሴት አትቍጠረኝ ብላ መለሰችለት። ዔሊም፦ በደኅና ሂጂ፥ የእስራኤልም አምላክ የለመንሽውን ልመና ይስጥሽ ብሎ መለሰላት። እርስዋም፦ ባሪያህ በዓይንህ ፊት ሞገስ ላግኝ አለች። ሴቲቱም መንገድዋን ሄደች፥ በላችም፥ ፊትዋም ከእንግዲህ ወዲያ አዘንተኛ መስሎ አልታየም።
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 1 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 1:12-18
9 ቀናት
የመጀመሪያው የሳሙኤል መጽሐፍ የእስራኤላዊት ሴት የሆነችውን የሐናን ታሪክ ይዘግባል። የሕይወቷ ሁኔታ ያስጎነበሳት እና ተስፋ አስቆራጭ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ግን እሷን ምሳሌ የምትሆን ፈሪሃ አምላክ ያላት ሴት አድርጎ ይገልጻታል። ይህ የንባብ እቅድ የሐናን የህይወት ታሪክ ለራሳችን ህይወት እንደ ምሳሌ ይወስደዋል። ከእኛ ጋር ያንብቡ።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች